የስቃይ ማስታገሻ (ማረሳሻ) መርፌ ከሞት አያድንም! ከአመታት በፊት "ቁጥር -2 ኢህአዴግ" ወደስልጣን ሳይመጣ አንድ በሆነ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምር ፕሮፌሰር ጋር በነበረን ውይይት ፥ ከታች ክፍል ስንማር መፅሀፍት ላይ የነበሩ ምሳሌዎችን በመውሰድ > እያለ ሲከራከረኝ ፥ በወቅቱ ሁኔታው የመሠለኝ ቀልድ እንጂ በዚህ በሁሉም ስርአቶች የግፍ ዶፍ በሚያስተናግድና አመድ አፋሽ በሆነ ህዝብ ላይ ፥ ያውም አንድ ትውልድ በመቅረፅ ላይ ባለ ምሁር ፥ በዚህ ደረጃ እስከ አጥንት ድረስ የዘለቀ ጥላቻና የተጠቂነት አስተሳሰብ ያዳብራል ብዬ አላመንኩም ነበር! ነገርግን አሁን በሁሉም መስክ በገሀድ የምናየው ፥ የታሪክ አጋጣሚ እየጠበቀ ለዘመናት የጥላቻ መርዝ እንደኒኩሌር ሲያብላላ የኖረው ፥ በሀሰተኛ ትርክት የሰከረ ፅንፈኛ የፖለቲካ ቡድን ፥ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያውን በፍፁማዊ ጭካኔ እየተጠቀመው ይገኛል! ከዚህ አኳያ የአማራ ህዝብ ሰለባ እየሆነ ያለበት ለአመታት የተረጨው ሀሰተኛ የጥላቻ ትርክት ሰንኮፉ እስካልተነቀለና "ህገ-መንግስት" በተሰኘው የሀገር ማፍረሻ ውል የተተከለበት ስርአታዊና መዋቅራዊ ግፍ ስርአታዊ በሆነ ለውጥ ካልተተካ ካሳለፈውም በላይ የመጪው ጊዜ ከበድ ያለ እንደሚሆን ቅንጣት አልጠራጠርም! ይህ የሚሆነው ደግሞ የአማራ ህዝብ ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ ሆኖ ፥ አንድነትና ህብረቱን ጠብቆ ፥ በጠራ የፖለቲካ ግብ ላይ በመመስረት እንደህዝብ የሞት ሽረት ተጋድሎ ሲያደርግ ብቻ ነው! አሁን ያለው የትግል አካሄድ "ከስቃይ ማስታገሻ መርፌነት" የዘለለ አንዳችም ጠብ የሚያደርገው ነገር የለም! 6.1K viewsedited 12:55