Get Mystery Box with random crypto!

በቆቦ ዙሪያ ወረዳ ወገኖቻችን ያሉበት ሁኔታ ይህ ነው! በብዙ ጭንቀት ውስጥ ሆነው የሚደርስባቸውን | ዘሪሁን ገሠሠ

በቆቦ ዙሪያ ወረዳ ወገኖቻችን ያሉበት ሁኔታ ይህ ነው!

በብዙ ጭንቀት ውስጥ ሆነው የሚደርስባቸውን ሰቆቃና ግፍ የሚነግሩንን የራያ ወገኖቻችን ድምፅ አለማስተጋባት ከቶውንም አይቻልም!

" ሲያወሩ ስንሰማቸው ‘ ተኩስ አቁም ላይ ነን’ ነው የሚሉን ፥ ላለፉት 15 ቀናት አልፎ አልፎ ተባራሪ ተኩስ ካልሆነ በስተቀር ምንም ውጊያ የለም!" የሚሉት በሰቆቃ ስር ያሉ የቆቦ ዙሪያ ወረዳ ወገኖቻችን ፥ ከሚደርስባቸው ድብደባና እንግልት ባሻገር የእርድ እንስሳቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ እያረዱ እንደሚበሉባቸው ፥ ዱቄትና የእህል ዘር የተባለን የአርሷደሮችን ስም ዝርዝር ይዘው ከየቤቱ በአህያ እየጫኑ እንደሚወስዱ ፥ በዱር የደረሱ ሰብሎች አተርና የእሸት እህሎችን ባሉበት እያወደሙ እንደማገኙ የገለፁ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ጨው እንኳ የተቸገሩበት ሁኔታ መኖሩን ይናገራሉ፡፡

" ከረሀቡ በላይ በየመንደሩ የታመሙና ከፍተኛ ህክምና የሚሹ ነዋሪዎች በቃሊም በኩል እንኳ አሳልፈን ለመውሰድ ብንሞክርም ሊፈቅዱልን ባለመቻሉ በሞትና በህይወት መካከል የሚገኙ ህሙማን ወደሞት አፋፍ እየተቃረቡ ነው!" ሲሉም ያሉበትን አስከፊ የጨለማ ህይወት ይገልፃሉ፡፡

የመከላከያ ሰራዊቱ በቃሊም በኩል አስገዳጅ ከሚባል አካባቢ ያለ ሲሆን በቅርብ ርቀት ደርባ ፣ አዋስ ፣ ደብረ ሰላም ፣ ቱሜ አስመላ ፣ ….ወዘተ የሚባሉ የቆቦ ወረዳ አካባቢዎችን ደግሞ ከ25-30 ሺህ የሚገመት የአሸባሪው ሀይል የነዋሪውን እህል እያወደመ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ላለፈው 15 ቀን ገደማም በዚያ በኩል ከተባራሪ ተኩስ ውጭ ምንም አይነት ውጊያ የለም፡፡

በዚህ መካከል ህዝቡ በረሀብ ፣ በህክምና እጦት እንዲሁም በሽብር ቡድኑ ጥቃት እያለቀ መሆኑን የሚናገሩት ወገኖቻችን ፥ " …ቢያንስ እነሱ ተኩስ አቁም እንደተስማሙት ሁሉ እኛም ታመው በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ልጆቻችንን ወደደሴ ወስደን እንድናሳክም ተስማምተው ሊፈቅዱልን ይገባ ነበር!" ሲሉ ሲቃ እየተናነቃቸው ይናገራሉ፡፡ ለማለፍ ያደረጉት በርካታ ጥረትም አልተሳካም፡፡

" መሳሪያ አላችሁ አምጡ እያሉ በየቤቱ በመዞር ከፍተኛ ድብደቢና እስር እየፈፀሙ እንደሚገኙ የሚገልፁት ታጋች ወገኖቻችን " መሳሪያ የለንም ስንል ደግሞ መሳሪያ ያለው ቤተሰባችሁ ሸሽቷልና ካለበት አስመጡ በማለት ደግሞ ዙረው ተመሳሳይ ግፍ ይፈፅሙብናል፡፡" ብለዋል፡፡

በቆቦ ዙሪያ ወረዳ 015 ቀበሌን ጨምሮ እስከሮቢት ድረስ ባሉ የወረዳው ቀበሌዎች በየአርሷደሩ በር ላይ የአሸባሪው ታጣቂዎች ጥብቅ ክትትል እያረጉ እንቅስቃሴአቸውን እየተቆጣጠሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

ትኩረት በእገታ ስር የመከራን ፅዋ ለሚጎነጩት የራያ ወገኖቻችን!