Get Mystery Box with random crypto!

የምትበላውን ስጧት ማርቆስ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴² ብላቴናይቱም የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረች | መንፈሳዊ ትረካ እና አጫጭር ጽሑፎች

የምትበላውን ስጧት
ማርቆስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴² ብላቴናይቱም የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረችና ወዲያው ቆማ ተመላለሰች። ወዲያውም ታላቅ መገረም ተገረሙ።
⁴³ ይህንም ማንም እንዳያውቅ አጥብቆ አዞአቸው፦ የምትበላውን ስጡአት አላቸው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ያስነሳትን ብላቴና "የምትበላውን ስጧት"
አላቸው! ሌሎች በመነሳቷ ደስታ ውስጥ ሆነው ያላስተዋሉትን ረሐቧን አውቆ የሚያስፈልጋትን ነገራቸው!
ጌታ ሆይ እኛም የምንበላው ያስፈልገናል ...ሰዎች እንዲሰጡን አንፈልግም አንተ ሁሉን ታውቅ አይደል ድጋሚ የማያስርብ የምንበላው ምግብ ያስፈልገናል።
ሌሎች እንደተራብነው የማያውቁት እኛም ያላስተዋነው ጉድለታችንን አንተው ሙላልን ርቦናል የምንበላው ስጠን።
የምንበላው ፍቅር ፣የምንበላው መተሳሰብ፣ የምንበላው ቸርነት የለንም ርቦናል የምንበላውን ከማያልቀው መሶብ በሰፊው መዳፍህ ዘግነህ ስጠን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
                                          25/09/14
                                            #zeboannerges