Get Mystery Box with random crypto!

አጋፋሪ፤ የሚለው መጠሪያ በ17ኛወና በ18ኛው ክፍለ ዘመን የታወቀ የቤተ መንግሥት ሹም መጠሪያ ነው | ዜና ቤተክርስቲያን

አጋፋሪ፤ የሚለው መጠሪያ በ17ኛወና በ18ኛው ክፍለ ዘመን የታወቀ የቤተ መንግሥት ሹም መጠሪያ ነው፡፡ ‹‹ህዱግ ራስ›› በመባል የሚታወቅም ነው፤ በቤተመንግሥት የሚካሄዱ ሥራዎችንና የፍርድ ሂደቶች ያስተባብራል፤ አንዳንዴ ደግሞ የክፍላተ ሃገር የፍርድ ሰጪ ሰዎች ስም ሆኖም ያገለግላል፤ የስሜን (ከጎንደር በስተሰሜን የሚገኝ ግዛት ነው) አስተዳደር የሚገዛ ሰው ደግሞ የሰሜን አጋፋሪ እየተባለም ይጠራል፤ (ለምሳሌም አፄ ሱስንዮስ ልጃቸውን ፋሲለደስን የስሜን አጋፋሪ ብለው ሹመወት ነበር፤ ይህ የስሜን አጋፋሪ የሚለው ሹመትም እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቆይቶ ነበር

ቡሄ
ቡሄ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት የነሐሴ 13 ቀን መጠሪያ ስሙ ነው የሚሉ ሊቃውንት እንዳሉ ሁሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤ ቡሄ የሚባለው፤ ከነሐሴ 13 በኋላ እስከ መስከረም 17 መስቀል ድረስ ሲሆን፤ በተለይም ይህ በዓል የሚታወቀው በሸዋና ወሎ /እስከ ጋይንት ጫፍ መጋጠሚያ) ድረስ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም ክርስትና አባት ለክርስትና ልጁ ተማሪ ከሆነ መጻሕፍትን (ዳዊት፣ …)፣ እንዲሁም አልባሳትን፣ በግና ሙክት ፍየልን የሚሰጥበት ነው፡፡ ሕፃናትና ወጣቱም ‹‹ቡሄ ፥ ሆ ….. ›› እያለ ይጨፍራል ፤ የሚሰጠውንም ሙክትና በግ እስከ መሰቅል ድረስ ሲያጠራቅም ከርሞ ለመስቀል ዕለት አርዶ ይበላል ፥ ደስታን ያደርጋል

ምንጭ፤ የቃል ትምህርት
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/