Get Mystery Box with random crypto!

ገና ምን አይተህ…! '…አዲስ አበባን የወረራት የኦሮሞ የገጠር ልጅ ነው። አዲስ አበባ አስተዳደር | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ገና ምን አይተህ…!

"…አዲስ አበባን የወረራት የኦሮሞ የገጠር ልጅ ነው። አዲስ አበባ አስተዳደር ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት እስከ ታችኛው አስተዳደር ድረስ ከወለጋ፣ ከአሩሲና ከባሌ፣ ከጅማ የመጣ ቄሮ ነው የሞላው። በሰፈሩ በደሳሳ ጎጆ ውስጥ ሕይወቱን ሲገፋ፣ ዋርካ ሥር እያደረ የኖረ ሰገጤ አዲስ አበባ መጥቶ ቅርስ፣ ታሪክ ብሎ ነገር የት አባቱ ያወረቅልሃል?

"…አሹቅ ስትበላ፣ ገንፎ ስታገነፋ የኖረች ኦሮምቲቲ ስለአንተ ባቅላባ ደንታዋ ነው ወይ…? የከብቶች ጩኸት ትዝታዋ የሆነ፣ ለፍቅር ሥራ ቁጥቋጦ ስትመርጥ የከረመች ባላገር ትዝታዋ ከገደልና ከጉድጓድ፣ ከጫካ ያልዘለለ ሰገጤ ስለአንተ የመኮንን ባር ባቅላባ ትዝታ፣ ስለ አንተ ታሪካዊ ሥፍራ ምን ደንታ አላት?

"…ከተሞች አይጽዱ፣ አይመሩ አይባልም፣ ቆሻሻ፣ የደከመ ሰፈር ቢታደስ፣ ቢጸዳ ምንም አይደል? ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ የኋለኛውን ዘመን የሚያስታውሱ ቅርሶችን ከቆሻሻ ሠፈር ጋር ማውደሙ ግን ጄኖሳይድ ነው። ሰገራና ሽንት በፌስታል የሚጠቀም፣ ሽንት ቤት የሌለው ሰፈርም ፈረሰ ማለት ትክክል ባይሆንም። ታሪካዊ ቤቶችን ማውደም ግን ልክ አይደለም።

"…ሰው በራብ በሚሞትበት ሀገር ሕዝብ አፈናቅሎ፣ ደሀ ለጅብ ሰጥቶ፣ መናፈሻ ካልሠራሁ ሞቼ እገኛለሁ ማለትም አግባብ አይደለም።

"…የፒያሳ ዶሮ ማነቂያ ሰፈሩ ሁሉ ቢፈርስ የመኮንን ባር ይፈርሳል ብዬ ግን በጭራሽ አላሰብኩም ነበር። የፒያሳ ልጆች ትዝታቸው እያዩት ተገደለ። ድራሽ አባቱን ነው ያጠፉበት። ገና ምን አይተህ ለገጣፎ ሲፈርስ ቆመህ ስትስቅ የነበርክ እሱን ጨርሰዋል አሁን በተራህ አንተን ያፈርሱሃል። ኀዘንማ በሁሉም ቤት ገና እኮ ይገባል።

• RIP… ፒያሳ…!