Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ' '…ሂሊኮፍተሯ ሥራ በዝቶባታል። ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ዋይዋይ ብትርፍ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ሂሊኮፍተሯ ሥራ በዝቶባታል። ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ዋይዋይ ብትርፍርፍ ስትል የምታድረው ሄሊኮፕተር አስከሬኗን እየለቀመች ነው። ዛሬም የዐማራ ፋኖ ቀንድሾ የጣለው አንድ ማንነቱ ያልታወቀ የጦር መኮንን ከጦር ኃይሎች ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በወታደሮች ታጅቦ አስከሬኑ በዚህ መልክ እየተሸኘ ነው።

"…እኔም የደመቀ መኮንን ከቢሮው መነሣት፣ የተመስገን ጥሩነህ ከቦታው መቀየር ወፎቼ አዲሱን ቤትና አዳዲሶቹን አለቆች አልለምድ ብለው ተቸገርኩ። አጎደሉኝ ከምር።

"…ብልፅግናም አይድንም…! …አመራሩም አይተርፍም። ሬሳህን ቁጠር። ሳታጯጩህ፣ ዜና ሳታስነግር፣ ሃገራቸውን አገልግለው አረፉ ሳትል ድምጽ አጥፍተህ ቅበር።

"…ለፋኖ ይሄ መንገድ ተስማምቶታል። አገዛዙ ደግሞ በፋኖ መገረፉን ማመኑን እንደ ውርደት ቆጥሮታል። ፋኖ ገደለኝ ማለትን እንደ ሞት ቆጥሮታል። ሃገራቸውን ለ30 ዓመታት አገልግለው በፋኖ የሞቱ፣ የተመቱ ወታደራዊ መኮንኖች ገበና እንዳይወጣ በሚል ሰበብ በክብር፣ በዐዋጅ መሸት፣ መቀበር ሲገባቸው ወሬ እንዳይሰማ ተብሎ እንደ ተራ ዜጋ በጓሮ በር በጓዳ ድምፅ ሳይሰማ እየተቀበሩ ነው። ይሄ ለወታደር ያውም ለመኮንኖች ትልቅ ውርደት ነው።

"…ዐማራ ክልል ትገባለህ ነገር ግን አትወጣትም። ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልም። አይቻልም። አይቻልም። በዚህ 4 ወር ብቻ ከ20 በላይ ኮሎኔል የተባለ እንደረረገፈ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት። የአዋሳውም ኮሎኔል በቤተሰብና በክልሉ መንግሥት ግፊት ነው ሞቱ ተነግሮ የተቀበረው።

• አዛኜን ዐማራ ያሸንፋል…!