Get Mystery Box with random crypto!

' ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸ | ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿

" ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው " - ቅዱስ ፓትርያርኩ

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን " ራስን በራስ የመሾም " አባዜ መገታት አለባቸው ሲሉ አሳሰቡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ በተካሄደው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ስርዓት ላይ ንግግር አሰምተው ነበር።

በንግግራቸው ላይም ፤ " በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው " ብለዋል።

" ማንኛውም ችግር በውይይትና በምክክር የተበደለውንም በትክክል በመካስ መፈታት ይገባዋል! " ያሉት ቅዱስነታቸው " ከዚህ ውጭ በጥፋት ላይ ጥፋት እየተከሠተ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተን ድርጊት ማቆም አለብን " ሲሉ አሳስበዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ቀኖና ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ባደረገው ጥረት፣ እንደዚሁም ኦርቶዶክሳዊው ሕዝበ ክርስቲያን ባቀረበው አቤቱታ ከዚህ ቀደም የተፈጸመው የቀኖና ጥሰት ታርሞ በዛሬው ዕለት ትክክለኛውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ቀኖናዊ ሕግን የጠበቀ ሥርዓተ ሢመት መከናወኑን የገለፁት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህ በመሆኑ " ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን " ብለዋል።

" ለወደፊትም ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት በሚጠቅም ጉዳይ ሁሉ ፤ በዚህ ዓይነት በውይይትና በምክክር ብቻ እየፈታን ሕዝባችን በመንፈስና በልማት የሚያድግበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በጋራ እንድንሰራ ጥሪያችንን እያቀረብን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።

(የቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)