Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን | ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿

በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለፁ።

የሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ዐባይ መለሰ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎቻችን በቦታው ለተገኘው ዘጋቢያችን ገልፀዋል።

ካህኑ በድንጋይ ተደብድበው እያሉ ምስልና ቪዲዮ ለማስረጃ ለመያዝ ቢሞክሩም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ሞባይል እየተሰበሰበ መሰረዙንም ነግረውናል።

@zemaryan
@zemaryan