Get Mystery Box with random crypto!

ምን አይነት ሚስጥር ነው? ስምሽን ስሰማ በደስታ የምሰክር ገመናዬን ሁሉ ላንቺ የማማክር ፍንድቅድ | የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

ምን አይነት ሚስጥር ነው?

ስምሽን ስሰማ በደስታ የምሰክር
ገመናዬን ሁሉ ላንቺ የማማክር
ፍንድቅድቅ የምለው ስትሆኚ ከጎኔ
ውብ የሚሆንልኝ በፈገግታሽ ቀኔ
ሳዝንም ስታዝኚ አብረሽ ስታነቢ
እኔ እንድጠግብ አንቺ ስትራቢ
ቀን በሄደ ቁጥር ፍቅርሽ የማይቀንስ
ሳቅሽ ትካዜዬን ህይወቴን የሚያድስ
ከምድር ከፍ አ'ርጎ ሰማያት የሚያደርስ
ምን አይነት ምስጢር ነው እማ የተቸረሽ
አድሮ የሚጨምር ልዩ እኮ ነው ፀጋሽ

ለእናትዬ
አይናለም
ግጥሟን ከወደዳችሁላት ሼር እና ላይክ ተባበሯት

ለመቀላቀል

t.me/zemaritnsae
t.me/zemaritnsae
t.me/zemaritnsae