Get Mystery Box with random crypto!

ቂያማ ለት አላህ ድኃ ባርያውን ጠርቶ እንዲህ ይለዋል፦‹‹በክብሬ እና በልቅናዬ እምልልኃለሁ፤ አን | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

ቂያማ ለት አላህ ድኃ ባርያውን ጠርቶ እንዲህ ይለዋል፦‹‹በክብሬ እና በልቅናዬ እምልልኃለሁ፤ አንተን ሳላከብርህ ቀርቼ አይደለም ዱንያ ላይ ድኃ እድርጌ ያኖርኩህ። እዚህ ያዘጋጀሁልህ ክብር እና ምንዳ ይበልጥልኃል ብዬ ነው

ባርያዬ ሆይ! ሂድ ወደ ህዝቡ ተገለጥ። ስለኔ ብሎ ያጎረሰህን እና ስለኔ ብሎ ያለበሰህን ለይተህ ወደ ጀነት ንዳቸው ››

ድኃው ባርያ ይህንን ካደመጠ በኋላ ወደ ህዝቡ ሲሄድ ፀሀይ ከአናታቸው የሚያፈላቸውን ህዝቦች በላቦቻቸው ተጥለቅልቀው ሲተራመሱ ያገኛቸዋል።

ዱንያ ላይ ያበሉትን እና ያለበሱትን እየለየ ከዝያ መከራ ይዟቸው ይወጣ'ና ወደ ቀዝቃዛይቱ ጀነት ያቀናል።

ይህን ሀዲስ ከተናገሩ በኋላ ረሱል ሰዐወ እንዲህ አሉ፦‹‹የድኃ ጓደኞችን አብዙ፤ የቂያማ ለት ግዛቱ የነሱ ነው'ና››

Sefwan Ahmedin