Get Mystery Box with random crypto!

ሰሀባዎች ዐረፋ ደርሶ ዒድ ከሰገዱ በኋላ ኡድሒያዎቻቸውን በማረድ ተጠምደዋል። አከባቢው ግርግሩ እና | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

ሰሀባዎች ዐረፋ ደርሶ ዒድ ከሰገዱ በኋላ ኡድሒያዎቻቸውን በማረድ ተጠምደዋል። አከባቢው ግርግሩ እና ትርምሱ የእርድ አጅሩን ለማግኘት በሚጣደፉ ሰሀባዎች ተሞልቷል።

ረሱል ሰዐወ ፍፁም እርጋታ በተሞላ ስሜት ውስጥ ሁነው ሁለት ቀንዳም በጎችን ይዘው ለማረድ ይዘጋጃሉ።

ሰሓባዎች ግራ ተጋብተዋል፤ "ኡድሒያ አንድ ሁኖ ሳለ እሳቸው እንዴት ሁለት ይይዛሉ" በሚል እየተብሰለሰሉ ነው።

ረሱል ሰዐወ በጉን አስተኙት፤ ቢለዋውን ከበጉ አንገት ላይም አሳርፈው ፍቅር እና ናፍቆት በቋጠረ አንደበት፦‹‹ጌታዬ! ይህ እርድ የኔ፣ የቤተሰቦቼ እና የእርድ አቅም ለሌላቸው የኡመቶቼ ኮታ ነው ተቀበለኝ›› ብለው ተክቢራት እያደረጉ አረዱት።

እንዴት ቢያፈቅሩን ይሆን ከቤተሰባቸው ተርታ ያሰለፉን!