Get Mystery Box with random crypto!

#አቡ_ሐሰን_ሙሀና ይሰኛሉ ። ህይወታቸውን ለአላህ የሰጡ ሰዎችን ወደ ጌታቸው እየተጣሩ የኖሩ የዳዕ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

#አቡ_ሐሰን_ሙሀና ይሰኛሉ ። ህይወታቸውን ለአላህ የሰጡ ሰዎችን ወደ ጌታቸው እየተጣሩ የኖሩ የዳዕዋ ሰው ናቸው ።

ከመኖርያ ቤታቸው በላይ በአላህ ቤት ረጅም ሰዓታትን ያሳልፋሉ ። ሰባት ልጆች አሏቸው ። ወንዶቹም ሴቶቹም ሁሉም የአላህን ቃል ቁርአንን በቃላቸው ሐፍዘዋል።

#ትላንት_በመጨረሻዎቹ የረመዳን አስር ቀናት በጋዛ ሰርጥ ፊታቸው እንዲህ ፈግጎ ከጌታቸው ጋር ተገናኙ። የሚያስደስታቸውን የአላህን ስጦታ እንዳዩ ነገር ጥርሳቸው ተፈልቅቆ እየሳቁ ሩሐቸው ከጀሰዳቸው ተላቀቀ።

[وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ مُّسْفِرَةٌ ضَاحِكَةٌ مُّسْتَبْشِرَةٌ]

"ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤ ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው" [ሱረቱል ዐበስ 38-39

አላህ ኻቲማችንን ያሳምርልን