Get Mystery Box with random crypto!

አንቺም .... አደባባይ ወጥቶ በማፍጠር ምን አገኘሽ ? እዛ ሂዶ ፎቶ ተነስቶ ከመምጣት በዘለ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

አንቺም ....

አደባባይ ወጥቶ በማፍጠር ምን አገኘሽ ?

እዛ ሂዶ ፎቶ ተነስቶ ከመምጣት በዘለለ ለእስልምናሽ የጨመረው እሴት ምንድነው?

እናት አባት እህት ወንድም የለሽም? .... ካለሽስ በላጩ ጌታሽ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ እነሱን ሃድመሽ ምታገኚው አጅር/ምንዳ ወይስ በአደባባይ መጮህ መሳለቁ ?

በረመዷን አንዲቷ ደቂቃ ዋጋ አላት ያቺ ደቂቃሽ ሰዓትሽን ያውም በጨለማ ምን ላይ አዋልሻት ?

አምሽተሽ ከ4-5 ሰዓት መግባትሽን እንደ እኩልነት ማየትሽ ይሄ ነው ኢስላም ላንቺ የዋለው ውለታ ? ወይስ አንቺ እስልምናሽን የምታሳዪበት ማንነትሽን የምትገልጪበት መንገድ ይህ ነው?

ቤተሰብሽን እምቢ ብለሽ ጎደና መውጣትሽን ከምን አንፃር ወደድሽው? .... ከምንስ አንፃር በላጭ ሆነልሽ?

ለእናትሽ አንድ ሲኒ ቡና ቀድቶ መስጠቱ ባልበለጠምን??

አንተም ....

በቻልክ በሆነልህና የእህትህን ነውር ደብቀህ ሰትረህ ባስዋብካት ባሳመርካት ነበር

ለሴት ልጅ ያለህን ንቀት የሆነችን ክፍተት ተጠቅመህ በአደባባይ ልታነውራት ባልተገኘችበት ባልዋለችበት ስሟን ምትጠራት አንተ ከየትኛዎቹ ጡሀራዎች ጎራ ሁነክ ነው ??

ለመሆኑ ባለገች ብለህ የምትጠራት ሴት የምትባልገው ብቻዋን ወይስ ካ'ንተ አይነቱ አደምይ ጋር ነው ??

አንተስ የእህትህን ክብር የምትጠብቀው በየትኛው በተከበረ ስፍራ ተገኝተህ ነው? ... ለመሆኑ አንተ አደባባይ የወጣኸው ልታፈጥር ወይስ ይህቺኑ እንስት ሽተህ??

አንተ ለእህትህ ለእናትህ ለሚስትህ ምን አይነት ወንድ ነህ?

እሷ ልታሳየው ያልቻለችው የኢስላም ክብር ባንተ በኩል ታየ ወይስ ምን ??

የት ውለህ ነው መዋያዋን የጠየቅካት ..? የት አይተሃት ነው የት ነሽን ያስከተልክባት ??

ብቻውን የባለገም ብቻዋን ያባለገችም የለችም