Get Mystery Box with random crypto!

የኳታር ዓለም ዋንጫ ድምቀት የሆነው ጋኒም አል-ሙፍታህ ጋኒም አል-ሙፍታህ ይባላል፤ የ20 ዓመት | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የኳታር ዓለም ዋንጫ ድምቀት የሆነው ጋኒም አል-ሙፍታህ

ጋኒም አል-ሙፍታህ ይባላል፤ የ20 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ የኳታር ዜጋ፣ Caudal Regression Syndrome (CDS) በተባለ ችግር ምክንያት ከወገብ በታች አካል የለውም።

እናቱ ከመወለዱ በፊት ልጇ ችግሩ እንዳለበት ተነግሯት በበርካቶች "ልጅሽን አስወርጂ" በሚል ብትመከርም፣ እናት ግን ጋኒምን ወልዳ ችግሩን አብራ መጋፈጥን መርጣለች።

ከአባቱ ጋር በመሆንም "ልጃችን ከወገቡ በታች አካል ባይኖረውም አንዳችን ቀኝ እግር፣ ሌላችን ግራ እግር እንሆንለታለን” ሲሉ ቃል በመግባት የዓለምን ፈተና አብረውት ለመታገል ቆረጡ።

የሚጋባ ፈገግታ የተቸረው ጋኒም በማኅበራዊ ሚዲያው ለሚሊዮኖች ንቃትን የሚፈጥር ወጣት ሆኗል።

ቀድሞ በጓደኞቹ ማንጓጠጥ ሊያቋርጠው የነበረውን ትምህርት ቀጥሎም በፖለቲካል ሳይንስ ዲግሪውን ለማግኘት እየተማረ ይገኛል።

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
http://youtube.com/@zekrmenzumaneshidatube

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

Join Tg
https://t.me/ZEKR_MENZUMA