Get Mystery Box with random crypto!

የእነዚህ ድድብ'ና ደግሞ ከልክ አለፈ። ጠያቂውም ተጠያቂውም ባለማሰባቸው የሚኩራሩ ደነዞች ሆኑ። አ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የእነዚህ ድድብ'ና ደግሞ ከልክ አለፈ። ጠያቂውም ተጠያቂውም ባለማሰባቸው የሚኩራሩ ደነዞች ሆኑ። አንዳቸው ከአንዳቸው የማይሻሉ ! በግልፅ ሃሳባቸው ምን እንደ ሆነ እንኳን በቅጡ አይገባም። ሰው እንዴት ምንም የማይገባ ነገር እየቀባጠረ ወንጌልን እየሰበክን ነው ብሎ ያምናል። የጠያቂውን ባለውቅም ነብዩ እንኳን ባለፈው 'ሞቼ ተነስቻለሁ...' ምናምን ሲል ሰምቼዋለሁ። እና ብሞትም መነሳቴ ስለማይቀር ምንም አታመጡም ብሎ ይመስለኛል ይሄን ያህል ርቀት ለብሽሽቅ ታጥቆ የተነሳው !
እኚ ሰዎች በሙስሊሙ ላይ ገደብ ሲያልፉ ይሄ የመጀመሪያቸው አይደለም። በቅርብ ከሰሩት ስህተታቸው እንኳን ሊማሩ አልፈለጉም። መጀመሪያ ባደረጉት ቃለመጠየቅ ነብይ ነኝ ባዩ 'ሙስሊሙ ነበርኩ ሊያውም ኢማም...' ምናምን ብሎ ብዙ ነገር ቀባጠረ። ግን ህዝቡ ቦታ አልሰጠውም። ይባስ አውቃለሁ በሚል ባወራቸው ነገሮች መሳቂያ ሆነ። የእስልምና እምነት ተከታዩም 'የተለመደ ድራማ ነው...' ብሎ ሙድ በመያዝ ብቻ ጉዳዩን አለፈው። የመጀመሪያው ስህተቱ ይሄ ይመስለኛል። እነሱ ግን በዚህ አላበቁም። ይሄን ከታለፍን አይቀር ብለው ጭራሽ መስመር አልፈው ተመለሱ። በብዙ ሚሊየን ህዝብ የሚከተላቸውን ፣ በናፍቆት የሚያለቅስላቸውን ፣ ከእራሱም ከአባቱም ከእናቱም በላይ አብልጦ የሚወዳቸውን ነብያችን (ሰአወ) በአደባባይ ይሳደቡ ጀመር !
ይሄ ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ በቀልድ የሚታለፍ ብቻ አይመስልም። መሆንም የለበትም። በሃይማኖት ጉዳይ ግጭት የሚፈጥሩ ነገሮችን መነጋገር ለማንም አይበጅም። አንድ አማኝ ከእራሱም ከሆነ ከብዙ ነገሮች አስበልጦ'ና አስቀድሞ ለሚኖርለት እምነቱ ለመሞትም ሆነ ለመግደል ቁርጠኛ ነዋ። ደስ እያለው ያደርገዋል። ይሄም ነገር ወደዚህ አይነት ሂደት ከማምራቱ በፊት የሚመለከተው የህግ አካል ሁለቱንም ይዞ ሊጠይቃቸው ይገባል።