Get Mystery Box with random crypto!

አጭር ማሳሰቢያ •••••••••••••• መስከረም 15 /2015 በሚሊኒየም አዳራሽ የሚደረገው 3ኛው | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

አጭር ማሳሰቢያ
••••••••••••••
መስከረም 15 /2015 በሚሊኒየም አዳራሽ የሚደረገው 3ኛው ዙር "በረሱል ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍቅር እና በመሻይኾቻችን መንገድ ሕያው ነን" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው መውሊድ ሰላማዊና ህጋዊ ሂደቱን የጠበቀ ፍፁም ሐይማኖታዊ ፕሮግራም ነው። ማህበራችን ከዚህ ቀደም ባለፉት ሁለት አመታት ተመሳሳይ ሁለት ሀገር አቀፍ መውሊዶችን በርካታ ህዝብ በተገኘበት አካሂዶ በሰላምና በፍቅር ሃይማኖታዊ ሥርአቱን ጠብቆ መጠናቀቁ የሚታወቅ ነው። የዘንድሮው 3ኛው ዙር መውሊድም ፍፁም ሃይማኖታዊ፣ ሰላማዊ እና ህጋዊ ሆኖ እንዲጓዝ ነሐሴ 20/2014 ለአዲስ አበባ መስተዳድር የእውቅና ፈቃድ ጠይቀን መስከረም 4/2015 ከመስተዳድሩ ህጋዊ እውቅና ለመውሊዳችን ተሰጥቷል።

በመሆኑም ማህበረሰባችን ይህን መውሊድ ለማስቀረት በሚፈልጉ አካላት ለሚረጩ ውዥንብሮች ቦታ ሳይሰጥ የመስከረም 15 መውሊድ በጉጉት እንዲታደም እናሳስባለን።

መንግስት ላደረገልን ቀና ትብብር እጅግ አድርገን እናመሰግናለን! መውሊዱ ሃይማኖታዊ ሥርአት ከመፈፀም ውጭ ሌላ ዓላማ እንደሌለው ለማሳወቅ እንወዳለን።

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCW7Mi9alF-Wnl9MRyll7g5A

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886