Get Mystery Box with random crypto!

የዳዕዋ ሰዎች ታላቁ ጀብድ የዳዕዋ ሰዎች ለኡመተል ኢስላም ከሚያበረክቱት ታላላ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የዳዕዋ ሰዎች ታላቁ ጀብድ


የዳዕዋ ሰዎች ለኡመተል ኢስላም ከሚያበረክቱት ታላላቅ አስተዋፆኦዎች መካከል ከዲን የራቁ ወንድሞችን ወደ ዲን ማምጣት ፣ ከመስጂድ የተኮራረፋትን ወደ መስጂድ ማምጣት ፣ ከአሏህ ጋር የተጣሉትን ማስታረቅ ነው ።

* ይህ ተግባር የትኛውም የሸሪአም ሆነ የቀለም ምሁር ፣ ሙፍቲ ፣ ኣቢድ የማይሰራው ከባድ ስራ ነው ። አሊሞችን ብንመለከት በአብዛኛው መጀመሪያም ዲን ውስጥ ሆኖ ኢልም መማር የሚፈልግን ሰው ነው የሚያስቀሩት ፣ የጠሪቃ ሸይኾችንም ብንወሰድ እንደዛው በብዛት እነርሱ ጋር መጥተው ተርቢያ የሚፈልጉ የዲን ሰዎችን ነው ተርቢያ የሚያደርጉት ።

( ይህን ስል የአሊሞችንን የተርቢያ ሸይኾችን ደረጃ ዝቅ ማድረጌ አይደለም ፣ ያለ ኡለሞች ሸሪአ እንደሌለ ግልፅ ነው ፣ የፈለገ ለዲን ብንሰራ ኡለሞችን ካልተከተለወን ወደ ጥሜት መሄዳችንም ግልፅ ነው)

* በቀላል አማርኛ የዳዕዋ ሰዎች ለሁሉም አይነት የዲን እንቅስቃሴዎች አገናኝ ኤጀንሲዎች ናቸው ፣ እነርሱ ወደ መስጂድ የማምጣቱን ትልቁን ድርሻ ከተጫወቱል ኢልም ማስተማሩና ተርቢያ ማድረጉ የአሊሞች ነው ።

* የዲን ስራ አንዱ አንዱን ያሟላል እንጂ አንዱ እንቅስቃሴ ብቻውን ሙሉ ዲን ሊሆን አይችልም ስለዚህ ከጭፍንተኝነት ወጥተን ለሁሉም እንቅስቃሴ እውቅና መስጠት አለብን ።
አንዳንዱ በዳዕዋ አማካኝነት መስጂድ ገብቶ አንድ ሁለት ኪታብ ይቀራና " እነዚህ የዳዕዋ ሰዎች ጃሂል ናቸው " ሲል ይስተዋላል አንዳንዱ የዳዕዋ ሰው ደግሞ " እገሌ ሸይኽ ጀውላ አይሰራም እንጂ ጥሩ ነበር " ሲል ይስተዋላል ፣ ሁለቱም እይታዎች ከጭፍንተኝነትና ከጥራዝ ነጠቅነት የሚመጡ የተሳሳቱ እይታዎች ናቸው ምክንያቱም ሁሉም ሰው የግድ በአንድ የዲን እንቅስቃሴ መሰማራት አይጠበቅበትምና ።

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ገንዘቡን ፣ ጊዜውን መስዋዕት አድርጎ የአሏህን ዲን ለመርዳት ቤት ለቤት ፣ ሃገር ለሃገር የሚዟዟሩ ለሊት ተነስተው ለኡመቱ የሚያለቅሶ ዳዒዎችን ከማየት በላይ የሚያስደስት ነገር የለም

https://t.me/ZEKR_MENZUMA