Get Mystery Box with random crypto!

#ክርስቶስ የኛ ጌታ ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው። ይህን ያህል ትዕግሥት እን | ዘቀራንዮ | ZEEKERANIO

#ክርስቶስ የኛ ጌታ

ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው። ይህን ያህል ትዕግሥት እንደ ምን ያለ ትዕግስት ነው። ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው። ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው። ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው። ፍቅር ያምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው። በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት ሕይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት። አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተሸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ። በአዳም ፊት የሕይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መጻጻን ጠጣ ወዮ።

የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው ምን ከንፈር ነው ምን አንደበት ነው። የፍቅር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ኅሊናም ይመታል ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል። የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ።

(የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ)

ዘቀራንዮ
13/8/2014
8:35pm
Dawit Deresa