Get Mystery Box with random crypto!

'ትንሿ ቤተ ክርስቲያን እንድትዳከም፣ እውነተኛ ቤተ ሰባዊ ሕይወት እንዲቀዛቀዝ ካደረጉ ነገሮች አን | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

"ትንሿ ቤተ ክርስቲያን እንድትዳከም፣ እውነተኛ ቤተ ሰባዊ ሕይወት እንዲቀዛቀዝ ካደረጉ ነገሮች አንዱ ባል (አባት) መሪነቱን በአግባቡ ባለ መወጣቱ ነው - ኃላፊነቱን በመዘንጋቱ!

"ብዙ ልጆች ከትዳር ውጪ የሚወለዱት፣ ባለ ትዳሮች ፍቺን እንደ ቀላል ነገር እንዲያዩት ምክንያት ከኾኑ ነገሮች አንዱ ባለ ራዕይ ባል (አባት) በማነሱ ነው፤ ባለ ራዕይ ባል (አባት) ሳይኾን ምድራዊ ምቾትን የሚፈልግ ወንድ በመብዛቱ ነው፤
ቤተ ሰብን ጣዖት አድርጎ የሚመለከት ወንድ በመብዛቱ ነው፡፡

"ኦርቶዶክሳዊ ወንድ ግን አግብቶ የሚኖር ከኾነ ባለ ራዕይ ባል (አባት) ወደ መኾን ማደግ ይኖርበታል፡፡ [ባለ ራዕይና ኦርቶዶክሳዊ ባል/አባት ራሱን፣ ሚስቱንና ልጆቹን አስቀድመው ጽድቁንና መንግሥቱን እንዲሹ በተግባር የሚመራ ማለት ነው፡፡]"

~ ትንሿ ቤተ ክርስቲያን፣ ገ. 313