Get Mystery Box with random crypto!

~ ወንጌል  ኦሪት እና ቁርኣን ~                       ምን ዓይነት ሕግጋት ናቸው ~ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

~ ወንጌል  ኦሪት እና ቁርኣን ~
                      ምን ዓይነት ሕግጋት ናቸው ~?

ክፍል-፩

ሙስሊሞቹ ራሱን ቁርኣንን መሠረት አድርገው በቁርኣን የተሰጠውን የሃይማኖት እና የሥነ-ምግባር  ሕግ የወንጌልም የኦሪትም የመጨረሻው አረጋጋጭ ሕግ እንደሆነ ያስተምራሉ(ቁርኣን 2:97 3:65 5:47 7:157)
ይህም የብሉይ ኪዳን ነብያት(ተውራት) እና የአዲስ ኪዳን(ኢንጂል) መጽሐፍት ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ቢሆኑም አሳሳቾች በርዘዋቸዋል ከእግዚአብሔር እንደተሰጠ ሳይበረዝ የተጠበቀ ትክክለኛ የኦሪት እና የወንጌል መጽሐፍ የለም ከሚለው በቁርኣን ጭምር የተነገረ እስላማዊ አስተምህሮ ጋር የተገናዘበ ነው።


የእስልምና የሥነ ምግባር ሕግጋት በክርስቲያኖች እንዴት ይታዩ እንደነበር እና በክርስትና-እስልምና ተዋሥኦዎች በተለየ ሁኔታ በተናጥል ይነሡ የነበሩ ጉዳዮችን እናያለን።

ለእልምና ትችቶች መልስ ከሰጡ ቀደምት ክርስቲያን ሊቃውንት መካካል ክርስቲያኑ ~አል-ኪንዲ~ የእስልምናን ሕግ ከክርስትና እና ከኦሪት ሕግጋት ጋር በማነጻጸር ይተቻል። የሊቁ ይህን ንጽጽራዊ ትችት የሚያቀርበው የኦሪትና የክርስትና መጻሕፍት ተበርዘዋል ለሚለው እስላማዊ ትችት መልስ ከሰጠ በኋላ በመሆኑ የእስልምና ሕግ(ቁርኣን) የቀደሙትን የሁለቱ ሕግጋት አስተምህሮ አረጋጋጭ ነው የሚለውን አይቀበልም።

አል-ኪንዲ ሦስት አይነት ሕግጋትን ይበይናል:-1 አምላካዊ ሕግ(the divine law) 2 ርቱዕ ተፈጥሯዊ ሕግ(the natural law) 3 ሰይጣናዊ ሕግ(the satanic law) ናቸው። አል-ኪንዲ  እነዚህን ሦስት ሕግጋት ካብራራ በኋላ የእስልምና ሕግ ከየትኛው የሚመደብ ነው? ብሎ ይጠይቃል።

አምላካዊ(የጸጋ) ሕግ ከፍጠረታዊ ሥርዓት አልፎ ሰውን እግዚአብሔርን የሚያስመስል ፍጹም ሕግ በመሆኑ አምላክ ሰው ኾኖ ያስተማረው እኔ አርአያ ኾኖ ያሳየው ሕግ ነው መገለጫውም የፍቅር እና ይቅርታ ከምላካዊ ርቱዕ ፍትሕ ጋር ሳይቃረኑ የሚገለጡበት መሆኑ ነው ይላል አል-ኪንዲ።
ይህ ሕግ የእግዚአብሔርን ጸጋ የተቀበሉ እና ክርስቶስን የሚከቱ አማኞች በፍቅር ሆነው የሚፈጽሙት ጠላትን ሳይቀር መውደድን የሚጠይቅ እና በሰማያዊ እና ዘላለማዊ ሕይወት ላይ የሚያተኩር ፍጹም ሕግ ነው። ይህ ሕግ የወንጌል ሕግ ነው።


ይቀጥላል ......


   ( "የልቦና ችሎት" በረከት አዝመራው  )  ይህን መጽሐፍ ብታነቡት ይበልጥ ታተርፍላቹሁ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ወንጌል ኦሪት  ቁርአን ምን አይነት ህግጋት ናቸው ሚለውን በምዕራፍ ከፍፍለን በተከታታይ ክፍል በፁሑፍ  እናቀርባለን ። ሼር  ለሌሎች እንዲደርስ በማድርግ እንድትከታተሉ መልእክቴ ነው ።

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

ኅዳር 15 2015 ዓ.ም