Get Mystery Box with random crypto!

| አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል | አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

| አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል |

አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል ።

የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲ
ታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል ። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስእለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው ።


የዮሴፍ ወድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር ፦ " በእውነት ወድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና ። ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን ።"/ ዘፍ 42*21/ ። ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል ፦ " ለጌታዬ ምን እንመልሳለን ? ምንስ እንናገራለን ? ወይስ በምን እንነጻለን ? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ ..."/ዘፍ 44*16/ ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኀላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው ።
ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡን ስላለፈ ኃጢአቱ  እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል ። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች " "እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ ። / 2ኛ ሳሙ 16*10/ በማለት በግልጽ ተናግሯል ።


ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን " ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ።" / ሚል 3*7/ እያለ ነው ። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው ።

ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና ።

| ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ፫ኛ |

https://t.me/akanim1wasen2