Get Mystery Box with random crypto!

የዐውድ አመት ራስ ዮሐንስ መስከረም-ሁለት ዛሬም የየራሳቸውን ጽድቅ እያቆሙ ጻ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የዐውድ አመት ራስ ዮሐንስ

መስከረም-ሁለት

ዛሬም የየራሳቸውን ጽድቅ እያቆሙ ጻድቃን ነን የሚሉ ይህን ትምክህታቸውን ትተው ወደ ጻድቃን ጥበብ ወደ ኦርቶዶክስ ጥበብ ይመጡ ዘንድ በዮሐንስ አምላክ እንጠራቸዋለን ። ዮሐንስ ለዚህ ሁሉ አገናኝ የፍቅር ገመድ ሆኗል ርእሰ ዐውድ ዓመት ዮሐንስ መባሉ ለዚህ ነው ። መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶት ፈቃዱን የሚሰራቸው አበው የዮሐንስ ዕረፍት መሰከረም ሁለት ቀን እንዲታሰብ አድርገዋል። ሙሉ ቀንም ያው የሚቆመው የማኅሌት ቃለ እግዚአብሔር ዮሐንስን የሚመለከት ነው ። ከእነዚህ "ርዕሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወለዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ " የሚለው ነው ። "አበቅቴንና መጥቅዕን የምትወልድ የዐውድ ዓመት ራስ ዮሐንስ " ማለት ነው ። ይህም ሶስት መሰረታዊ ትርጓሜያት አሉት፦

የመጀመሪያው የዐውድ ዓመት ራስ የሚለው ነው ። ዛፍ ያድግ ያድግና ጫፍ ላይ ፍሬን ይቋጥራል ። ዓመቱ የአመቱ መጨረሻ ላይ መስከረም አንድ ቀን እንደ ፍሬ ይቀመጣል። የዮሐንስም ትንቢት ነብያት ሲዘራ ኖሮ ዮሐንስ በነቢያት መጨረሻ እንደ ፍሬ ተቀምጧል ።


ሁለተኛ መስከረም አንድ ቀን የዓመቱ አጽዋማት በዓላትን የሚወጡበት የሚቀመሩበት አበቅቴን መጥቀዕ የሚወጡበት ዕለት ነው ። ዮሐንስም "ዕለት ኅሪት - የተወደደች የጌታ ቀን ዓመት " በምትባለው በዘመነ ሐዲስ ለሚደረገው የጽድቅ ስር ሁሉ አበጋዝ ፈት አውራሪ ወጣኒ መንገድ ጠራጊ ቃለ አዓዲ ነውና።


ሶስተኛው መስከረም አንድ ቀን ያለፈው ዓመትና የመጣው ዓመት የሚገናኝበት ድልድይ ነው። ዮሐንስም ትንቢተ ነቢያትን ስብከተ ሐዋርያትን መሀል ላይ ያገናኘ ነውና ርእሰ ዐውድ ዓመት ተባለ።



( ርዕሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን    "ጸያሔ ፍኖት")


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ


JOINE JOINE



https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe