Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት | @𝐀𝐛𝐮𝐟𝐞𝐰𝐳𝐚𝐧[Official Channel]

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለ1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልአድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ምክርቤቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በዓሉ የሠላም ፣ የአንድነት ፣ የመቻቻልና የፍቅር እንዲሆን ተመኝቷል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ በዓልን ሲያከብር ካለው ላይ ቀንሶ ለሌላቸው በማካፈል በዓሉን በጋራ እንዲያከብርም ጥሪ ቀርቧል።
የኢድ ሶላት በነገው እለት በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም እንደሚከበር የገለፀው ምክር ቤቱ ÷ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 2:30 ድረስ ሃይማኖታዊ ስርዓቱ ተከናውኖ እንደሚጠናቀቅ አስታውቋል።
በዚህም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የፀጥታውን ጉዳይ እንዲያስጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።
ህዝበ ሙስሊሙ ክረምቱ መግባቱን ተከትሎ የአረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርቧል።