Get Mystery Box with random crypto!

#ከጠላት_ፈተናዎች_ተጠንቀቅ! ዲያቢሎስ ቀስቱን ሲወረውርብንና በውጊያው ሲያውከን ይህ በእኛ ላይ | ሊቀ መዘምራን

#ከጠላት_ፈተናዎች_ተጠንቀቅ!

ዲያቢሎስ ቀስቱን ሲወረውርብንና በውጊያው ሲያውከን ይህ በእኛ ላይ ብቻ የተደረገ ቁጣና ጠላትነት አይደለም፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔርም ጠላት ነውና በእኛ ላይ ሚደርሰው መከራ በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ተቃውሞ ነው። ዲያቢሎስ እግዚአብሔርን ማጥቃት ባለመቻሉ ፍጥረታቱን በማታለልና ከእርሱ ከእርሱ ጋር ወደ ዘላለማዊ ቅጣት እንዲገቡ በማድረግ ሊበቀለው ይጥራል፡፡

የተወደድኸው ሆይ! ይህንን ነገር አስተውል! ዲያቢሎስን ስትቃወመውና ስትዋጋው ክፉን ነገር ከእናንተ እያራቅህ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየተዋጋህ ነው፡፡ ስለዚህም የክፉውን ዲያቢሎስ ዲያቢሎስ ማማለያና መደለያ በመቀበል እግዚአብሔርን ከማሳዘን ይልቅ ፈተናውን በጽናት ስትታገል በውጊያው ላይ ብትሞት ይሻልሃል፡፡

ለአፍታም ቢሆን ብቻህ እየተዋጋ እንዳለህ አድርገህ አታስብ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላትህ ላይ ድል መንሣትን ይሰጥሃል፡፡ "አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ፡፡ ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቆጣው? በልቡ:: አይመራመረኝም ይላልና፡፡" (መዝ ፲ ፥ ፲፪ -፲፫) ጥሩርና ጋሻ ያዝ፤ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡ ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት።›› (መዝ. ፴፭፥፪-፫)

"አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ፡፡ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ  አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።" (ኢሳ. ፫፥፩-፪)

በነፍሳችን ላይ ደካማነትን እስካላየ ድረስ ሰይጣን አያጠቃንም፡፡ ጎበዝ አዳኝ ወፎችን ለማደን እንደሚያደርገው ዲያቢሎስም ወጥመዱን ለማስገባት ሁልጊዜ ከእኛ ላይ ቀዳዳን ይፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜም ይዋጋናል፣ ይሸነግለናል በምኞቶቻችንም እየገባ ያገኘናል፡፡

አዳምን በሔዋን፣ ሶምሶንን በምወድደው ደሊላ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በእንግዶች ሴቶች ፍቅር፣ የአስቆሮቱ ይሁዳንም በገንዘብ ፍቅር እንደጣላቸው አላየህም፡፡ ስለዚህ እንደ ጎበዝ ሐኪም ሁን፣ ጉድለትህንና ሕመምህንም አክም፤ ኩራትህን በትሕትናና በየዋህነት ድል አድርገው፣ የትዕቢት በሽታህንም አንተነትህን በመናቅ ፈውሰው፡፡ በተአምራትና በታላቅ ነገሮችም ከመመካት ተጠበቅ ምክንያቱም ዲያቢሎስ ራሱ በብርሃን መልአክ መመስል ይችላል፡፡ በስብ ውስጥ መርዙን ሊከት፣ በማጥመጃው ዘንግ ውስጥም የመደለያ ጣፋጭ ምግብን ሊያደርግና መልካምና ጠቃሚ ነገር ይከተላል ብለህ እንድታምን ሊያታልልህ ይችላል፡፡ አንተ ግን ፈጽሞ አትታለል፣ በከንቱም አትነዳ፡፡ ይልቅስ ከዲያቢሎስ ጥቃት ትጠበቅ ዘንድ ሁሉን ነገር አስተውልና መርምር፡፡

ይሁዳ ጌታውን አልከዳምን? ኢዮአብስ ወዳጅና የሚታመን ሰው መስሎ አሜሳይን አልገደለውምን? (፪ነገ. ፳ ፥ ፱)

በእግዚአብሔር ታመን! ከመሪ በላይ አጥብቀህ ያዘው፤ ሁሉን ነገር ወደ እርሱ አምጣው፡፡ ድጋፍህና መጠጊያህ አድርገው፤ እርሱ ሁለንተናህ አድርገው።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

@Z_TEWODROS
@Z_TEWODROS
@Z_TEWODROS

Comment @Channel_admin09