Get Mystery Box with random crypto!

#ሶርያዊው_ቅዱስ_ኤፍሬም ስለ #ጌታ_ትንሣኤ በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ አለ፦ አቤቱ ገነትንና በ | ሊቀ መዘምራን

#ሶርያዊው_ቅዱስ_ኤፍሬም ስለ #ጌታ_ትንሣኤ በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ አለ፦

አቤቱ ገነትንና በውስጧ ያሉትን የሚገልጽልኝ ሕግህ መርከቤ ነው፤ መስቀልህ ይህንን ገነት የሚከፍትልኝ የገነት መክፈቻ ቁልፍ ነው። ከለመለመው ስፍራ፣ ከገነትም አበባ፣ ጽጌረዳ እና ሽታው ጣፋጭ የሆኑን በእቅፌ ሰብስቤ አመጣሁ። እነሆ የትንሣኤህን በዓል ስናከብር እነዚህን አበባዎች ጎዘጎዝንልህ። ይኸውም ልብን ደስ የሚያሰኙ ማኅሌትና ዝማሬዎች ናቸው። አክሊላትን ለሚያቀዳጅ ለእርሱ ምስጋና ይገባል።

በዚህ በዓል ላይ በደስታ የተሞሉ የሴቶችና የወንዶች፣ የወጣቶች ድምፆች እንደ መለከት፤ የሕፃናት መዝሙሮችም እንደ በገና ድርድር ነው። ድምፃቸውም የጌታቸውን ምስጋና ይዞ ወደ ሰማይ ይወጣል። ዝምታውም ከመባርቅት በላይ ለሚሰማ ለእርሱ ምስጋና ይገባል።

እነሆ መሬት ከታች ድምፅዋን አሰማች፤ ሰማያትም ከላይ ከመባርቅት ድምፅ ጋር ጉርምርምታን አሰሙ። ሚያዝያ ሁለቱን ድምፆች አንድ ላይ አፈለቀች። እነዚህ ድምፆችም ከላይ የተሰሙ እና ከታች የተደመጡ ናቸው። ከቤተ መቅደስ የሚሰማው ምስጋናም ከመለኮታዊው ድምፅ እና ከመልካም መቅረዞች በሚንቦገቦጉት መብራቶች፣ እንደ ዝናብ ከሚፈስ ዕንባ ጋር የፋሲካውን በዓል እናከብራለን።

(#ድርሳነ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ - ገጽ 275-276 ትርጉም ዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

@Z_TEWODROS
@Z_TEWODROS
@Z_TEWODROS

Comment @Channel_admin09