Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ሆይ! በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተ | ሊቀ መዘምራን

ሰው ሆይ!

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ" በማለት ተናገር። አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስቲ ከፍ ካለው ተራራ፤ ከታላቁ ባህር ፤ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና። ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን? አይመስለኝም።

(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ የነፍስ አርነት መጽሐፍ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•