Get Mystery Box with random crypto!

#ወዳጄ_ሆይ! ገንዘብ የለህምን? ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርግ፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘ | ሊቀ መዘምራን

#ወዳጄ_ሆይ! ገንዘብ የለህምን? ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርግ፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ የምታደርግ ከኾነ ገንዘብ ካላቸው በላይ ባለጠጋ ነህ፡፡ “እንዴት?” ትለኝ ይኾናል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- የእነዚያ (የባለጠጐቹ) ገንዘብ ያልቃል፡፡ ያንተ ግን ብል አይበላውም፡፡ ጊዜ አይለውጠዉም፡፡ አያልቅም፡፡ ወደ ሰማያት፣ ወደ ሰማየ ሰማያት፣ ወደ ምድር፣ ወደ አየራት፣ ወደ እንስሳቱ ዓይነት፣ ብዙ የብዙ ብዙ ወደሚኾኑት ዕፅዋት፣ ወደ ደቂቀ አዳም በጠቅላላው፣ ወደ መላዕክት፣ ወደ መላዕክት አለቆች፣ ወደ ኀይላት ተመልከት፡፡ እነዚህ ኹሉ የአምላክህ ፍጥረቶች ናቸው፡፡ የእነዚህን አምላክና መጋቢ ባሪያ መኾን ድኻ መኾን አይደለምና ድኻ አይደለህም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

#ተወዳጆች_ሆይ! ቀናትን ቈጥሮ በዓል ማድረግ የክርስቲያን ግብር አይደለም፤ የአሕዛብ ግብር እንጂ፡፡ እንዴት? የክርስቲያኖች ተፈጥሮ በቀንና በወር የተገደበ አይደለምና፡፡ አገራችን ሰማይ ነው፡፡ ግብራችን ሰማያዊ ነው፡፡ ኅብረታችንም ከሰማያውያን መላዕክት ጋር ነው፡፡ በዚያ መዓልት ለሌሊት ስፍራውን አይለቅም፡፡ ሌሊትም በተራው ለመዓልት አይለቅም፡፡ እዚያ ኹሌ መዓልት ነው፡፡ እዚያ ኹል ጊዜ ብርሃን ነው፡፡ ስለዚህ “ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ” እንደተባልን ኹል ጊዜ ማሰብ ያለብን ይህንን ነው (ቈላስ.3፡1)፡፡ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮአችን ከዚህ ምድራዊ አቈጣጠር በላይ ነው፡፡ በንጽህና በቅድስና እየኖርን ዘወትር በዓልን የምናከብር ከኾነም የዚሁ ዓለም ሌሊት ለእኛ ሌሊት አይደለም፤ መዓልት ነው እንጂ፡፡ ዘመናችንን በሙሉ በገቢረ ኀጢአት፣ በስካር፣ በዘፈን የምናሳልፈው ከኾነ ግን መዓልቱ ለእኛ መዓልት አይደለም፤ ሌሊት ነው እንጂ፡፡ ፀሐይዋ ብትወጣም ልቡናችን ገና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይኖራልና ቀን እንደወጣ አይቈጠርም፡፡

#ሰማዕትነት_አያምለጣችሁ መጽሐፍ ገጽ 13-19
via ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•