Get Mystery Box with random crypto!

#ጠቃሚ_ምክር_ከቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ 'ባልንጀራህን ልትገሥጽ ብትፈልግ፣ ልትመክር ብትሻ፣ ወይም | ሊቀ መዘምራን

#ጠቃሚ_ምክር_ከቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ባልንጀራህን ልትገሥጽ ብትፈልግ፣ ልትመክር ብትሻ፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ልታደርግ ብትፈቅድ ይህን ያለ ቍጣና ከስሜታዊነት ወጥተህ አድርገው፡፡ የሚገሥጽ፣ የሚመክር ሰው ባለ መድኃኒ ት ነውና፡፡ ነገር ግን ለራሱ ባለ መድኃኒትን የሚሻ ከኾነ ሌላውን ሰው እንደ ምን መፈወስ ይቻለዋል? ራሱ ቁስለኛ ኾኖ ሳለ ሌላውን ለመፈወስ ከመኼዱ በፊት የራሱን ቁስል የማያሽረው ለምንድን ነው? ባለ መድኃኒት ሌላ ሰውን ለማዳን በሚኼድበት መጀመሪያ የራሱን እጅ ያቆስላልን? የሌላውን ዐይን ለማዳን የሚኼድ ባለ መድኃኒት አስቀድሞ የራሱን ዐይን ያሳውራልን? እንዲህ ከማድርግ እግዚአብሔር ይጠብ ቀን፡፡

ስለዚህ አንተ ሰው! ሌላውን ከመገሠጽህና ከመምከርህ በፊት የራስህ ዐይኖች አጥርተው የሚያዩና ንጹሃን ይኹኑ፡፡ ሕሊናህን አታቆሽሸው፡፡ እንዲህ ከኾነ ግን ሌላውን ማንጻት እንደ ምን ይቻልሃል? በቍጣ ውስጥ መኾንና ከቍጣ ንጹህ መኾን የሚሰጡት ውስጣዊ ሰላም በጭራሽ የሚነጻጸር አይደለም፡፡ እንዲህ ከኾነ ታዲያ ሰላም የሚሰጥህን ጌታ [ነፍስህን] አስቀድመህ ከዙፋኑ ላይ ጥለህና ከጭቃው ጋር ለውሰኸው ስታበቃ፡ ከእርሱ እርዳታን የምትሻው እንዴት ብለህ ነው? ዳኞች የዳኝነት ሥራቸውን ሊያከናውኑ ሲፈልጉ አስቀድመው ካባቸውን ደርው ከፍርድ ዙፋናቸው ላይ እንደሚቀመጡ አላየህንምን? አንተም ነፍስህን የዳኝነት ልብስን አልብሰሃት በተገቢው ቦታዋ ልታስቀምጣት ይገባሃል፡፡ እርሱም የማስተዋል ልብስ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 62-63)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•