Get Mystery Box with random crypto!

'የአምላክ እናት ድንግል በነፍስም በሥጋም ቅድስት የሆንሽ ሆይ አስጸያፊና የቆሸሽኩ፣ በዝሙትና በክ | ሊቀ መዘምራን

"የአምላክ እናት ድንግል በነፍስም በሥጋም ቅድስት የሆንሽ ሆይ አስጸያፊና የቆሸሽኩ፣ በዝሙትና በክፉ ሥራዬ ነፍሴንና ሥጋዬን ወደ አሳደፍኩ ወደኔ ተመልከች፤ እመቤቴ ሆይ በከንቱ ነገርና በሥጋዊ ፍትወት የነደደውን ሕሊናዬን ንጹሕ አድርጊልኝ፡፡

የታወረ እና ከርታታ የሆነውን ሐሳቤን እንዳይደለል አድርጊው፡፡ እመቤቴ ሆይ ራሴን እንድቆጣጣር፤ ሕዋሳቴንም እንድመራቸው እርጂኝ። ከተያዝኩበት አስቀያሚ ሕይወትና ከሚያስጨንቀኝ ክፉ ሥራ ሁሉ ነፃ አድርጊኝ።

በውስጤ የሚመላለሰውን የኃጢአት ሥር ሁሉ በጣጥሺልኝ፤ ጎስቋላ የምሆን እኔን ሕሊናዬን የጋረደውን ገፈሽ ቀናውን መንገድ የምጓዝና የተረጋጋሁ አድርጊኝ፡፡ ከኃጢአት ጨለማ አላቀሽ አንቺን ከፍ አድርጌ እንዳመሰግንሽ እርጂኝ። እውነተኛ ብርሃን የሆነው የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ሆይ የሚታዩ እና የማይታዩ ፍጥረታት ሁሉ ከልጅሽ ጋር አንቺን ያመሰግኑሻል።"

(#ድርሳነ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ - ገጽ 215
#በዲያቆን_መዝገቡ_ከፍያለው)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
     •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•              
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌‌‌