Get Mystery Box with random crypto!

የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) እና የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 17 ቀን | ሊቀ መዘምራን

የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) እና የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅደስት ሥላሴ ካተድራል እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) መግለፃቸውን የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ለረጅም ጊዜ በሀገር ውስጥ እና በውጭ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ትላንት ከዚህ ዓለም በሞተ ስጋ መለየታቸው መገለፁ ይታወቃል።

ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ/ም ምሽት ነበር ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።

ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ ከ፲፯ ዓመታት በፊት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእረ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አንብሮተ ዕድ የተሾሙ ነበሩ።

ብፁዕነታቸው አስኬማ መላእክት ከሚለበስበት የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ሲያገለግሉ እንደነበር ታሪካቸው ያስረዳል።

ብፁዕነታቸው በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በመንበረ ጵጵስና ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከአገልጋይነት እስከ የበላይ ጠባቂነት በአባትነት አገልግለዋል።

ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ነበሩ።

tikvahethiopia
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌