"ኪዳነ ምሕረት እናቴ" | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ኪዳነ ምህረት እናቴ ምስጢረኛ ጓዳዬ የጎደለኝን ታውቂያለሽ ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ (፪) አዝ...... አልፏል መናኛው ኑሮ ምልጃሽ ውኃውን ቀይሮ መልካሙ ወይን ደረሰ እንባዬ ባንቺ ታበሰ (፪) አዝ......... ልዘምር ልቁም ከፊትሽ ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ ብርቅ ከሀገር ከቤቴ ከቶ አልረሳሽም እናቴ (፪) አዝ........ አልልም መቼ ነው ቀኑ የኔ መጎብኛ ዘመኑ እንደሚፈፀም አውቃለው ሁሉን በጊዜው አያለው (፪) አዝ........ የልቤን ችግር ላዋይሽ ከስዕልሽ ፊት ቆሜ እንባዬ ቀድሞ ዝም አልኩኝ ሳልነግርሽ ስለምታውቂ (፪) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE •✥• @abenet_tmhert •✥• •✥• @z_tewodros •✥• ✥ @abenet_tmhert •✥• ✧━━━━━━━━━━━✧ 1.9K views◦•●Yaredo●•◦, edited 18:30