Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም! ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ለዛሬ ፊታችን ላይ የሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን እንዴት ማስወ | ዩስሪ ሂና ዲዛይን Yusri Hinna design ወራቤ

ሰላም! ውድ የቻናላችን ተከታታዮች

ለዛሬ ፊታችን ላይ የሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን እንዴት ማስወገድ ይቻላል? የሚል ይሆናል ርእሳችን እነሆ;

ፊታችን ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን በተለያዩ መንገዶች ማስወገድ ይቻላል።

ፈታችን ላይ የሚወጡ እነዚህ አላስፈላጊ ነገሮች ለቆዳችን ጤና ጠንቅ ከመሆናቸው ባሻገር ውበታችን እንዲቀንስ ያደርጋሉ። እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት ለማስወገድም በቀጣይ የተዘረዘሩትን ማስወገጃ መንገዶች ተግባራዊ በማድረግ ከፊታችን ላይ ማስወገድ እንችላለን፡፡

☞ቫይታሚን ሲ

ቫይታሚን ሲ ፊትን ከአላስፈላጊ ጥቁር ነጠብጣቦች ለመከላከል አይነተኛ መንገድ ነው፡፡
ቫይታሚን ሲ ማለትም እነ ቡርትካን፣ሎሚ፣እስትሮበሪ፣ፓፓያ፣ብሮኮሊ፣ማንጎ፣አናናስ፣አረንጓዴ ቃሪያ.....እነዚህ ፍራፍሬዎችን መመገብም ሆነ ከቫይታሚን ሲ ፍራፍሬ ውህድ የተሰሩ የተለያዩ ውጤቶችን በመጠቀም ያማረና ፅዱ ቆዳ እንዲኖረን በእጅጉ ያግዘናል፡፡

☞ ኮጂክ አሲድ

ኮጂክ አሲድ ቆዳን ከማንፃቱ ባሻገር ቆዳችንን ከፀሃይ ለመከላከል ያስችላል ፤ በእንጉዳይ የበለፀገ በመሆኑም
ለቆዳ ተስማሚ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡

ኮጂክአሲድን በተለያየ መንገድ በገበያ ላይ ማግኘት እንችላለን፤
ለምሳሌ በሳሙና፣በዱቄት፣በክሬም፣በመድሃኒት መልኩ ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን።

☞አኩሪ አተር

ሌላው የጠቆረ ቆዳን ለመከላከል የሚጠቅሙን ከአኩሪ
አተር የተሰሩ የተለያዩ መከለከያ መንገዶች እናገኛለን።
ይህም ጥቁር ቆዳን በማንጻት ያማረ የፊት ቆዳ እንዲኖረን ያግዘናል፡፡ ጠዋት እና ማታም የጠቆረ ቆዳችንን በመቀባት ማስወገድ እንችላለን።

☞አዚሊክ አሲድ

አዚሊክ አሲድ ገብስ፣አጃ እና ስንዴ ከመሳሰሉ
ጥራጥሬዎች የሚገኝ ሲሆን፥ ቆዳችን ከጥቁር ነጠብጣብ የፀዳ እና ያማረ እንዲሆን ይረዳናል፡፡

በተጨማሪም ፊታችን ላይ ከሚወጡ ጥቁር ጠባሳዎችን ከማጥፋት ባሻገር ፊታችን ላይ ያሉትን ባክቴሪያዎች ያስወግድልናል ፡፡

ይህንንም በቀን ሁልት ጊዜ በመጠቀም ለውጡን ማየት
እንችላለን፡፡

☞የፀሃይ መከላከያ ክሬም(sun creame)

የፀሃይ መከላከያ ክሬም ፊታችን ያማረ እንዲሆን ከሚረዱን መንገዶች አንዱ ሲሆን፥ ቆዳችንን ከሚጎዱ
ነገሮችም ይከላከላል ፡፡
ክሬሙን ሁልጊዜ በመጠቀምም ፊታችን ከመሸብሸብ ብሎም ከጥቁር ነጠብጣቦች መጠበቅ እንችላለን፡፡
ነገር ግን የክሬም ምርጫችን ለፊት ቆዳችን ተስማሚ መሆን አለበት
@yusri_hinna