Get Mystery Box with random crypto!

የምስጋና በዓል ጥሪ ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የኃያላን መቅደስ ቤተ ክርስትያን ከእግዚአብሔር | Y4C

የምስጋና በዓል ጥሪ

ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

የኃያላን መቅደስ ቤተ ክርስትያን ከእግዚአብሔር በተቀበለችው ተልዕኮ መሠረት በቃሉ እና በመንፈሱ የታጠቁ ኃያላንን ማፍራት የጀመረችበት ሰባተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል የፊታችን ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓም በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በዓሉ የሚከበረው እግዚአብሔር ለራዕዩ ማረፊያ ይሆን ዘንድ በሰጠን ሰፊ ቦታ ላይ መሆኑ ምስጋናችንን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል።

በመሆኑም በተዘጋጀው የምስጋና ድግስ ላይ የራዕዩ ቤተሰቦች፣ ከራዕዩ የተጠቀማችሁ፣ በእግዚአብሔር መንግሥት አብሮ ሠራተኞች እንዲሁም ደስ ካላቸው ጋር ደስ የሚላችሁ ቅዱሳን በሙሉ እንድታደሙ በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል።

ጧት- 3፡00 -7:00 ከስአት 10:00-2:00

አድራሻ - ከኃያት አደባባይ ወደ 72 በሚወስደው መንገድ ዙሪያሽ ሞል ፊት ለፊት