Get Mystery Box with random crypto!

. .. ~~~~ #እርም_በል_አርመን °°° °° ° ፖለቲካን መሰል ፥ ምን ግም አለ ከንቱ ? ስ | ዮቶጵ ኢትዮጵያ

.
..
~~~~ #እርም_በል_አርመን
°°°
°°
°

ፖለቲካን መሰል ፥ ምን ግም አለ ከንቱ ?
ስልጣን እና ወንበር
ይሄዳል ይመጣል ፥ ሰዎች እየሞቱ ።

እድሜ ሳይወስነው ....ፆታ ወይ ማንነት
በደም መነካካት ...መወጋጋት በእምነት
የሚያስጎነጉነን ....ሊዶለን ከሙታን
ፖለቲካ...... ጅኒ
ፖለቲካ ........ሸርጣን

ዜሮ ብዜት አለም....ስጋዊ መበደል
ትርፉ ከሰው ማጣት
ትርፉ ከሰው መጉደል
እያለባበሰ የሚሸነግለል ፥ አፈ ቅቤ ጠብደል
ፖለቲካ....ቁማር
ፖለቲካ ....ደለል
የመኖር ቁልቁለት ...የድሀ ሰው ገደል !!!

* / / / / ***

መሰላሉን_ላክልን_አንድዬ

አብርሀም_ተክሉ

ከ #ግጥምብቻ @Getem

@Yotop77
@Yotop77
@Yotop77