Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ቅኔ!! የያዝኩት ደመና ፥የነካውት እንደ ጉም ተኖ እንደ ጭስ ከእጄ እንዳዋራ በኖ ውሃን | ቢንያም ፀጋዬ

የእናቴ ቅኔ!!

የያዝኩት ደመና ፥የነካውት እንደ ጉም ተኖ
እንደ ጭስ ከእጄ እንዳዋራ በኖ
ውሃን እንደመውቀጥ፥ ምግባሬ ከንቱ ሆኖ
ህይወት እነደ እንዝርት ፥ከቶ ስታዞረኝ
ባአሳር እንግልት፥ እልፉን አሳይታኝ
በደረስኩበት ተናካሽ ውሻ እንዳየ፥ ከቶ ስታሮጠኝ
ከእናቴ እልፍኝ ተገኘሁ፥ ቅኔዋን ስቀኝ

የሰማውን ምጣድ፥ አሟሽታ አዙራ
አስሳ አዙራ አዙራ፥ አስፍታ እንጀራ
አከምባሎ ስትከድን ፥ምጣዱ ላይ በድኑን
ላቧን የጠረገች ፥ስትቆሰቁስ ፍሙን
የቅኔዋን ፍቺ፥ አገኘሁት ወርቁን

ህይወት እንደ ምጣድ ፥አሳይታ ስፍራ
ሰውን በፈተና ፥እንደ አብሲት አዙራ
የእንግልት በድን ፥ስጭን በየጎራ
ትዕገስት የሌለው ሰው፥
አይጎርስም የረሱን እንጀራ

ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP