Get Mystery Box with random crypto!

ሞት አፈረ!! መኖር ባይቻለኝ፥ ዘላለሜን በምድር እንደ ተራራ ገዝፎ፥ ከነግርማ መኖር እንደ ንፋስ | ቢንያም ፀጋዬ

ሞት አፈረ!!

መኖር ባይቻለኝ፥ ዘላለሜን በምድር
እንደ ተራራ ገዝፎ፥ ከነግርማ መኖር
እንደ ንፋስ በምድር፥ ዘላለሜን መዞር
የእድሜ ጣራዬ፥ ቢያንስ ከነማቱ ሳላ
በወሰን ስፍር ተበጅቶ ኬላ
ከጀምበር ጋ ሲጠልቅ፥ እድሜ ሆኖ ጥላ

በዘመድ አፍቃሪ ፥በወዳጅ ጓደኛ
ለግዜው ስዘከር፥ ገላፈር ሲተኛ
#ሞት ሆይ አይንህን ላፈር
በጳጉሜ እድሜ ፥በኖርኩባት ምድር
በሰራውት ስራ ስሜ ሳይቀበር
ከመቃብር በላይ ፥ዘላለም ነው የምኖር

ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP