Get Mystery Box with random crypto!

DSTV ስንሠራ ሁሌ የሚያጋጥመን ችግር      _   ከትች  የምትመለከቱት ፎቶ DSTV ስትሠሩ | YøÑi SªT { ዮኒ ሳት } የመረጃ ቻናል



DSTV ስንሠራ ሁሌ የሚያጋጥመን ችግር
     _
  ከ
ትች  የምትመለከቱት ፎቶ DSTV ስትሠሩ ኳሊቲ ካመጣችሁ በዋላ በፋይንደር ነገር ግን ሪሲቨሩ ላይ Search ስታደርጉ እንዲህ ብሎ ይፅፋል። እናም በተደጋጋሚ እየደወላችሁ ለጠየቃችሁኝም መልስ ይሆናል።
DSTV ለመስራት ፈጣን Transponder  12245 v/H 27500 ነው። Horizontal አድርጋችሁ የምትሠሩ ከሆነ የግድ የLNB አቀማመጥ (ገመድ  የሚገባበት ቁልቁል ወደ መሬት ነው)። ይህ የመጀመርያው ሲሆን በመቀጠል DSTV የሚገኘው Eutelsat 36°B ነው። ይህ ሳተላይት ደግሞ ከናይል ሳት ወደ ግራ ከዲሹ ጀርባ በመሆን ቀና በማድረግ ወደ ግራ እጃችሁ መውሰድ ነው።ከዛን በዚህ ቁጥር  እስከ 85 ድረስ በቀላሉ ይመጣል።
  በመቀጠል ሪሲቨራችን ላይ በ 11919V 27500  Free ቻናሎች ማለትም የሀገራችን ቻናሎች ከከፈቱ አልያም Search ስታደርጉ ከገቡ ትክክለኛ የDSTV ሳተላይትን ሠርተናል ማለት ይቻላል።
  ይህ ከላይ ያለው ፁፍ ከመጣላችሁ ግን
1 ትክክለኛ የDSTV ሳተላይት አልሠራችሁም በፋይንደር ኳሊቲ ቢመጣም ሌላ ሳተላይት ከሆነ
2 ገመዱ ችግር ካለበት
3Connector  ስትገጥሙ ስህተት ካለው ብቻ ስለሆነ  ከዚህ በዋላ ስትሠሩ ይህ ፁፍ ከመጣ ከላይ የሚገኙትን ነገሮች ተመልከቱ።

                 DSTV ሪሲቨር እና የPackage አይነቶች
             __

DSTV ጎጆ  በወር 220 ብር የምንከፍል ሲሆን ከ70 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ።
DSTV ቤተሠብ በወር 380 ብር የምንከፍል ሲሆን ከ 100 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ።
DSTV ሜዳ በወር 550ብር የምንከፍል ሲሆን ፕሪሜርሊግን ጨምሮ ከ 130 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ።
DSTV ሜዳ ፕላስ ደግሞ በተሻለ ሁኔታ 160 ቻናሎችን የምታገኙ ሲሆን 1300 ብር በወር ትከፍላላችሁ።
DSTV ፕሪሚየም በወር 2600ብር የምትከፍሉ ሲሆን ከ170 በላይ ቻናሎችን የምታገኙብ Package ነው።