Get Mystery Box with random crypto!

3ኛው ዙር ጠቅላላ የቲቪ እንዲሁም የሪሲቨር ጥገና ስልጠና __ በዚኛው ዙር በአዲስ መል | ዮናስ ሳተላይት ዲሽ እና ኤሌክትሮኒስ

3ኛው ዙር ጠቅላላ የቲቪ እንዲሁም የሪሲቨር ጥገና ስልጠና
__
በዚኛው ዙር በአዲስ መልክ ጠቅላላ የቲቪ( Crt + Flat) እንዲሁም የሳተላይት ሪሲቨር ጥገና ስልጠና ለመስጠት ተዘጋጅተናል። በዚህም ስልጠና ላይ ጠቅላላ የቴሌቭዥን ትምህርት ከመጀመርያው እስከ መጨረሻ እንዲሁም የሪሲቨር የSoftware እና Hardware ጥገና ትምህርቶችን ያካትታል።
ስልጠናው በዚኛው ዙር ምን የተለየ ነገር አለው ?
በዚኛው ዙር ስልጠና ከዚህ በፊት ከተዘጋጁት ቪዲዮዎች በተጨማሪ አዳዲስ ቪዲዮዎችን ያዘጋጀን ሲሆን ስልጠናውም በሁለት አይነት መንገድ መከታተል ይቻላል።
ስልጠናውን ለመከታተል ጠቅላላ የቲቪ ጥገና ስልጠና 1500.00 ብር ብቻ ሲሆን ይህም Crt እና Lcd Led ቲቪን ያካተተ ነው። የሪሲቨር ስልጠና መከታተል የምትፈልጉ ደግሞ 500ብር ብቻ በመክፈል የስልጠናው አካል መሆን ይቻላል።
ስልጠናውን በሁለት አይነት መንገድ ያዘጋጀን ሲሆን ይህም Internet መጠቀም የምትችሉ ለሠልጣኞች ብቻ በተከፈተው Private የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል በሳምንት አራት ቀናት የምንለቃቸውን ቪዲዮዎች በቀላሉ በመመልከት መከታተል የምትችሉ ሲሆን እያንዳንዳቸው ቪዲዮዎች 07:00_12:00ደቂቃ ርዝመት ያላቸው Highly compressed የሆኑ ከ 35_45Mb የሚደርሱ ቪዲዮዎች ናቸው።
ስልጠናውን ለመከታተል Internet አገልግሎት የምትቸገሩ ደግሞ ጠቅላላ የስልጠናውን ቪዲዮ 16Gb ፍላሽ ላይ አድርገን በፖስታ በ3 ቀናት ያላችሁበት ድረስ በመላክ ፍለሹን በመውሰድ በቤታችሁ ቲቪ ላይ :ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ በማገኛኘት በ Full Hd ጥራት መከታተል ትችላላችሁ። በፍላሽ የምትፈልጉ ሠልጣኞች የፍላሽ 300ብር ብቻ በመጨመር መላኪያውን በራሳችን አድርገን የምንልክ ይሆናል።
ስልጠናው ምን ያህል ጊዜ ይቆያል ? የክፍያው ሁኔታስ ?
እንግዲህ ከዚህ በፊት በነበሩን የስልጠና ጊዜያት ስልጠናው 2 ወራት አካባቢ የመጀመርያው ዙር የቆየ ሲሆን በአሁኑ የስልጠና ጊዜ ግን ወደ አንድ ወር የተቀየረ ሲሆን ይህም የሆነው ቪዲዮዎች የሚለቀቁበት ቀናት በሳምንት አራት ቀኖች ስለሆነ ነው። ስለሆነም ስልጠናውን መከታተል የምትፈልጉ በ1 ወራት ውስጥ ብቁ የሆነ የኤሌክትሮኒስ ባለሙያ መሆን ይቻላል።
የክፍያው ሁኔታ የቲቪ ስልጠና የምትከታተሉ በአንድ ጊዜ ማከናወን ወይም በሁለት ዙር ክፍያችሁን መጨረስ ትችላላችሁ። ጠቅላላ የቲቪ ስልጠና ክፍያ 1500 ብር ብቻ ሲሆን በሁለት ዙር ማጠናቀቅ የምትፈልጉ ደግሞ የመጀመርያ ክፍያ 750ብር በመክፈል ከዛን በስልጠናው ላይ እያላቹ መሀል ላይ ደግሞ ቀሪውን ክፍያ መፈፀም ይቻላል። ነገር ግን ለሪሲቨር ሠልጣኞች ክፍያው አንድ ዙር ብቻ ሲሆን እሱም 500ብር ብቻ ነው።
በዚህ ስልጠና ለመከታተል ገንዘብ ገቢ ስታደርጉ ደረሰኝ ፎቶ በመላክ ወይም Mobile banking ከሆነ ደግሞ Screenshot በመላክ መመዝገብና ቀጥታ ስልጠናውን መጀመር ትችላላችሁ። ባለፈው ጊዜያት በነበሩት የስልጠና ሠአቶች በጠቅላላ ከ 58 አካባቢ የሚደርሱ ሠልጣኞችን አሠልጥነን የጨረስን ሲሆን በአሁኑ ሠአትም እየወሠዱ የሚገኙ ወደ 22 ሠልጣኞች ይገኛሉ።
ገንዘብ ገቢ ለማድረግ ከታች በሚገኙት የባንክ አካውንቶች መጠቀም ይችላሉ
1000139090822 - ንግድ ባንክ
01320263863800 - አዋሽ ባንክ
5052913428001 - ዳሸን ባንክ ዮናስ ገረመው ።
ተጨማሪ መረጃዎቻችንን ደግሞ አብዛኞቻችሁ በምታውቁን Youtube እንዲሁም ትሌግራም ቻናላችንን ይጠቀሙ
Youtube - www.youtube.com/YonsatTech
Telegram - @YONASDISH2 * @YONASDISH
Phone - +251930756350 * +251964644627

ማረጋገጫ ከታች የሚገኙትን የሠልጣኞችን ደረሰኝ በጥቂቱ ፖስት አድርገናል ይመልከቱ

በቤትዎ በመሆን የሙያ ባለቤት ይሁኑ !