Get Mystery Box with random crypto!

Yidnek Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ yidnek_tube — Yidnek Tube Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yidnek_tube — Yidnek Tube
የሰርጥ አድራሻ: @yidnek_tube
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 64

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-09-27 09:20:32
ኮምፒውተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ (Crash) የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች!
.
.
.
63 viewsYidnekachew Shiferaw, edited  06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 10:39:25 • ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድና የተከበራችሁ የ'Yidnek Tube' የቴሌግራም ቻነል ቤቴሰቦች! •

× ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት አብዛኞቻችን ስማርት ስልክ (Smarphone) አለን፤ ነገርግን የት ሀገር ምርት (Product) እንደሆነ ብዙም ዕውቀቱ የለንም።

× ያንን በማስመልከት ዛሬ ከ20 በላይ ስማርት ስልኮች (Smartphones) የት ሀገር እንደሚመረቱ እናያለን፤ አብራችሁኝ ቆዩ!


፩. iPhone (አይፎን) - የአሜሪካ ምርት

፪. Google Pixel (ጉግል ፒክስል) - የአሜሪካ ምርት

፫. Motorola (ሞቶሮላ) - የአሜሪካ ምርት

፬. Microsoft (ማይክሮሶፍት) - የአሜሪካ ምርት

፭. Samsung (ሳምሰንግ) - የደቡብ ኮሪያ ምርት

፮. LG (ኤልጂ) - የደቡብ ኮሪያ ምርት

፯. Huawei (ሁዋዌ) - የቻይና ምርት

፰. Lenovo (ሌኖቮ) - የቻይና ምርት

፱. Vivo (ቪቮ) - የቻይና ምርት

፲. Oppo (ኦፖ) - የቻይና ምርት

፲፩. Xiaomi (ሺያዎሚ (ሻሚ) ) - የቻይና ምርት

፲፪. One Plus (ዋን ፕላስ) - የቻይና ምርት

፲፫. Infinix (ኢንፊኒክስ) - የቻይና ምርት

፲፬. Realme (ሪያልሚ) - የቻይና ምርት

፲፭. Redme (ሬድሚ) - የቻይና ምርት

፲፮. Tecno (ቴክኖ) - የቻይና ምርት

፲፯. iTel (አይቴል) - የቻይና ምርት

፲፰. Asus (አሱስ) - የታይዋን ምርት

፲፱. HTC (ኤችቲሲ) - የታይዋን ምርት

፳. Lava (ላቫ) - የህንድ ምርት

፳፩. Sony (ሶኒ) - የጃፓን ምርት

፳፪. Nokia (ኖኪያ) - የፊንላድ ምርት


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube
66 viewsYidnekachew Shiferaw, edited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 21:09:18
#ዜና_ቴክ
#Tech_News

× እንኳን ደስ አላችሁ ዩቲዩበሮች!
× Congra Youtubers!

× ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው የዩቲዩብ ቻነል ኖሮን በዩቲዩብ Community ለማስከፈት 1000 Subscribers ይጠይቅ ነበር።

× ነገር ግን አሁን ዩቲዩብ አሻሽሎት 1000 Subscribers የነበረውን ወደ 500 Subscribers ዝቅ አድርጓል።

× ይሄ ደግሞ ለጀማሪ ዩቲዩበሮች በጣም ምርጥ የሆነ ነገር ነው።

× ስለዚህ በዩቲዩብ Community ከቀጣይ ጥቅምት ወር ጀምሮ ማለትም ከOctober 12, 2021 ጀምሮ 500 Subscribers እና ከዛ በላይ ያላችሁ ዩቲዩበሮች መጠቀም ትችላላችሁ።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube
79 viewsYidnekachew Shiferaw, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-16 22:20:29
ለስኳር ታማሚዎች ቆሽትን ተክቶ የሚሰራ ቴክኖሎጂ ሊቀርብ ነው!

× የዓይነት 1 የስኳር በሽታን መቆጣጠር የሚያስችል ሰው ሰራሽ የቴክኖሎጂ ሙከራ ላይ አስደናቂ ውጤት መገኘቱ ተሰማ፡፡

× ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው ይህ መሳሪያ በሰውነት ቆዳ ውስጥ በሚቀበሩ ሴንሰሮች አማካኝነት ቆሽታቸው ኢንሱሊን ማምረት ያቆመ የስኳር ታማሚዎችን (የዓይነት 1 የስኳር ሕመም ተጠቂዎችን) የስኳር መጠን ባለማቋረጥ የሚከታተል ይሆናል ነው የተባለው፡፡

× አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በቆሽት አማካኝነት አስፈላጊው የኢንሱሊን መጠን በደም ስሮች እንዲሰራጭ ትዕዛዝ ይሰጣል ተብሏል፡፡

× መሳሪያውን ታማሚዎቹ የደም ስኳር መጠናቸውን ለመለካት ፣ ለመቆጣጠር የሚወስዱትን ጊዜ ፣ በአጋጣሚ የስኳር መጠናቸው ዝቅ ብሎ ለሕይወታቸው አስጊ ሆኖ ቢገኝ ወደ ሕክምና እንኪደርሱ የሚደረሰውን ጉዳት ያስቀራልም ነው የተባለው፡፡

× እስካሁን ድረስም የዓይነት 1 የስኳር ሕመም ያለባቸው 1ሺህ ሰዎች ተለይተው የመቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂው እየተገጠመላቸው መሆኑን ዴይሊ ሜይል አመላክቷል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube
89 viewsYidnekachew Shiferaw, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 21:41:22 #ስለ_Google_አስር_የሚያስደንቁ_ነገሮች
#10_Amazing_Facts_About_Google

× ስለጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች እነሆ!

፩. ስያሜው

- ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል

-ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።

- በእንግሊዝኛው "googol" ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።

- እናም ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው ፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።

፪. የጀርባ ማሻ

- የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው "Backrub" ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።

- ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ ፤ ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።

፫. የተንጋደደ

- ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።

- እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።

፬. ፍየሎች

- ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል ፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው።

- አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ ፤ ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።

፭. እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'

- ጂሜይል ፣ ጉግል ማፕ ፣ ጉግል ድራይቭ ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

- ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ ፤ አንድሮይድ ፣ ዩትዩብ ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።
ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።

፮. ዱድል

- "ዱድል" የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።

- ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።

- አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።

፯. ለሌሎች ያመለጠ ዕድል

-በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።

-ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።

- አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል ፤ ሚሊዮን አላልንም ፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።

፰. መሪ ቃላት

- "ከይሲ አትሁን" ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።

- "ምን አገባው" የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።

፱. ምግብማ ግድ ነው

- ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።

- የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።

፲. የጉግል ባልንጀራ

- የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።

- ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube
76 viewsYidnekachew Shiferaw, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 18:56:07 Channel photo removed
15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 18:50:03
#ስለ_Google_አስር_የሚያስደንቁ_ነገሮች
#10_Amazing_Facts_About_Google
59 viewsYidnekachew Shiferaw, 15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 11:25:41 → Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube
60 viewsYidnekachew Shiferaw, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 11:25:38
#መረጃ_የሚሰርቀው_የቻርጀር_ገመድ

× ማርክ ግሪን የተባለ የደህንነት ተመራማሪ "OMG" የተሰኘው የቻርጀር ገመድ የተጠቃሚውን መረጃ በመውሰድ ወደ ሌላ ቦታ እንዲያስተላልፍ አድርጎ መስራቱ ተነገረ፡፡

× ይህም ገመድ በተለይ ሀከሮች ከተለያዩ ኮምፒውተሮችና የሞባይል ስልኮች ላይ የሚፈልጉትን መረጃ ማስተላለፍ እንዲችሉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡

× ገመዱ ከተሰካበት ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ ያሉ የይለፍ ቃላትንና ሌሎች ምስጢራዊ መረጃዎችን ለመመንተፍ ሁነኛ ዘዴ ተደርጎም ተወስዷል፡፡

× ከዚህ በፊት የነበረው "ላይትኒንግ" የተሰኘው ገመድ ስልኮቻችንን ከኮምፒውተር ጋር በማያያዝ ሀይል መሙላት የሚያስችል የነበረ ሲሆን ማርክ ግሪንና ጓደኞቹ ለዚህ ገመድ ማሻሻያ አድርገውለታል፡፡

× አሁን ላይ ገመዱ መረጃን አከማችቶ ከመያዝ በተጨማሪ በውስጡ በተገጠመለት የWiFi ቺፕ አማካኝነት መረጃውን ወደ ሌሎች ቦታዎች ማስተላለፍ ይችላል፡፡

× ማርክ ግሪን ይህንን ገመድ በዚህ መልክ ያሻሻለበትን ምንያት ሲናገር በቴክኖሎጂው ዙሪያ ያሉ ሰዎች ይህን ማድረግ አይቻልም የሚል እምነት የነበራችው በመሆኑ ፤ በተለይም መረጃን ለማከማቸት እና ለማስተላለፍ የሚረዱ ቁሶችን በገመዱ ውስጥ መግጠም ያስቸግራል ስለሚሉ ይህ እንደሚቻል ለማሳየት እንደሆነ ተናግሯል፡፡

× አንድ ሰው ይህን ገመድ በመጠቀም ስልኩን ቻርጅ ሲሞላ ወይም መረጃ ሲያስተላልፍ ገመዱ ስራውን ውስጥ ለውስጥ ይሰራል፡፡

× ይህም የሚያሳየን የምንጠቀማቸውን ኬብሎች ምንነት መለየት እንዳለብን ነው፡፡

× በተለይ ከፍተኛ የሆኑ ሀገራዊ ተቋማትና ድርጅቶች ውስጥ የምንጠቀማቸው የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ምንነት በሙያተኛ ተጣርቶ መጠቀም ይገባናል፡፡
66 viewsYidnekachew Shiferaw, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ