. . . በዓለማችን ላይ ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው ፲ (አስር) አስገራሚ ድረ-ገጾች! | Yidnek Tube
.
.
.
በዓለማችን ላይ ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው ፲ (አስር) አስገራሚ ድረ-ገጾች!
× በአሁኑ ወቅት መጠኑ ይለያይ እንጂ አንዳንዶቻችን በየቀኑ የኢንተርኔት መረቦችን መቃኘታችን የተለመደ ተግባር ሆኗል።
× የምንቃኛቸው ድረ-ገጾችም ብዙ ጊዜ የምናውቃቸውን አልያም በጣም ታዋቂዎቹን ነው።
× አንዳንድ ጊዜም በፌስቡክ ወይንም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ያገኘናቸው መረጃዎች አዳዲስ ድረ-ገጾችን ያስተዋውቁናል።
× እነዚህን አዳዲስ ድረ-ገጾችም ጠቃሚ ሆነው ስናገኛቸው ለሌላ ጊዜ እንድንጠቀማቸው ቡክማርክ አድረገን እናስቀምጣቸዋለን።
× ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 10 ድረ-ገጾች ግን ምናልባትም አይተናቸው የማናውቃቸው እና የተለየ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።
፩. 10Minutemail.com
× ይህ ድረ-ገጽ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የኢ-ሜይል አድራሻ ለመክፈት ያስችላል።
× ድረ-ገጹ የተላላክናቸውን መልዕክቶች እና የኢ-ሜይል አድራሻውን ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል።
× 10Minutemail.com እንደከፈትነው ምንም ምዝገባ ሳያስፈልገን ራሱ የኢ-ሜይል አድራሻ ይሰጠናል።
× በተጨማሪም Tempmail ለዚህ ይጠቅመናል።
× አጠራጣሪ ድረ-ገጾች ስንከፍት ኢ-ሜይል ሲጠይቁን በዚህ መጠቀም እንችላለን።
፪. Fake Name Generator
× በጣም ዓይናፋር የሆኑ ፣ የግል ጉዳያቸው የሚያስጨንቃቸው እና ትክክለኛ ስማቸውን ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ ሰዎች በዚህ ድረ-ገጽ አማካኝነት የሀሰት ስም እና ዝርዝር መረጃዎችን መፍጠር ይችላሉ።
፫. Down for Everyone or Just Me
× አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተርዎ የተወሰኑ ድረ-ገጾችን አልከፍት ሊልዎት ይችላል።
× እናም በዚህ ድረ-ገጽ አማካኝነት እውን ይህ ድረ-ገጽ አልከፍት ያለዎት ስለማይሰራ ነውን? አልያስ ሆን ተብሎ እንዳይከፍቱት ስለተደረገ ነውን? የሚለውን ማረጋገጥ ይችላሉ።
፬. Date and Time
× በዚህ ድረ-ገጽ ደግሞ በቀናት እና በዓመታት መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለማስላት ይጠቅማል።
× ለአብነትም ዕድሜያችን በቀናት ለማስላት የተወለድንበትን ቀን ፣ ወር እና ዓመት እና የዕለቱን ቀን ፣ ወር እና ዓመት በማስገባት በምድር ላይ ለስንት ቀናት ቆይታ እንዳደረግን ማስላት እንችላለን።
× የምናሰላው ቀን በዓላትን እና የሳምንቱን ቀናት ማለትም ቅዳሜ እና እሁድን አካቶ አልያም ሳያካትት ስንት እንደሆነም ማወቅ ያስችላል።
፭.. Web Capture
× የተለያዩ ድረ-ገጾችን የፊት ገፅታ ምስል ለማስቀረት እና ወደ JPG ወይምJPEG ፣ PNG አልያም PDF ፎርማት ለመቀየር ይህን ድረ-ገጽ ይጠቀሙ።
፮. Google NCR
× የጉግል ድረ-ገጽን ወይም google.comን ስንከፍት ጉግል ወደ ያለንበት ሀገር ዶሜይን ያስገባናል።
× ለምሳሌ ጉግልን በኢትዮጵያ ስንከፍት google.com.et ወደሚለው ያሸጋግረናል።
× ይህም የሚሆነው ጉግል እንደየሀገራቱ የሚከለክለው እና የሚፈቅደው ህግ ስላለው ነው።
× እናም ጉግልን ያለምንም የሀገራት ገደብ ለመክፈት google.com/ncr ብለን መፈለግ በቂ ነው።
፯. Virustotal
× ከጓደኞቻችን አልያም ከማናውቀው ግለሰብ የሚያጠራጥር ፋይል ከተላከልን እና ከኢንተርኔት በቀጥታ ያወረድነውን ፋይል በዚህ ድረ-ገጽ አማካኝነት የተላከልን ፋይል ወይም ዳውንሎድ ያደርግነው ፋይል ቫይረስ መያዙን እና አለመያዙን ማወቅ እንችላለን።
× ቫይረስቶታል ነፃ የኢንተርኔት የቫይረስ መመርመሪያ (ስካነር) ነው።
፰. IPviking
× በዓለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የመረጃ ምንተፋዎች ፣ የአይፒ አድራሻዎች ፣ የመረጃ ዘራፊዎቹን (የሃከሮቹን) አድራሻ እና የመሳሰሉ መረጃዎችን http://map.norsecorp.com/#/ በተባለው ድረ-ገፅ ላይ መመልከት ይቻላል።
፱. Hackertyper
× ይህን ድረ-ገፅ ከፍተን የተለያዩ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ስንጫን መረጃ ዘራፊዎች ወይም ሃከሮች የሚጠቀሙበትን ዓይነት ገጽ ይከፍትልናል።
× በዚህም ጓደኞቻችን እና ወዳጆቻችን የተለያዩ ድርጅቶችን መረጃዎችን እየሰረቅን ለማስመሰልና ለመሸወድ እንችላለን። (ግን ሀላፊነቱን እኔ አልወስድም ፤ ተጠንቀቁ!)
፲. Password Generator
× ጠንካራ እና በቀላሉ ብሬክ የማይደረግ ማለትም የማይሰበር የይለፍ ቃል ለፌስቡክ ፣ ለኢ-ሜይል እናም ለሌሎች ፓስዎርድ ለሚጠይቁ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሙሉ ጠንካራ የይለፍ ቃል ወይም ፓስዎርድ ለመመስረት ይረዳናል።
→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group
→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube