Get Mystery Box with random crypto!

. . . ፩. የሃርድዌር (Hardware) መቃረን - ለዊንዶውስ (Windows) ክራሽ የማድረግ | Yidnek Tube

.
.
.

፩. የሃርድዌር (Hardware) መቃረን

- ለዊንዶውስ (Windows) ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የሃርድዌር መቃረን ነው።

- እያንዳንዱ ሃርድዌር ክፍሎች ለመግባባት IRQ (Interrupt Request
Channel) ያስፈልጋቸዋል።

- እነዚህ IRQ ለየሃርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው።

- ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1 ነው ያለው።

- እያንዳንዱ ሃርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል።

- ግን ብዙ የሃርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሃርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሃርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ።

- በዚህም ሰዓት ሁለት የሃርድዌር
ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል።


፪. የተበላሸ ራም (RAM)

- ራም (Ram ወይም Random-Access Memory) ችግሮች ዋናው የብሉ ስክሪን ኦፍ ዴዝ (Blue
Screen of Death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልዕክት
'ፋታል ኤክሰፕሽን ኢረር' (Fatal Exception Error) የሚል ነው።

- 'ፋታል ኤክሰፕሽን ኢረር' የሚነግረን አሳሳቢ የሃርድዌር ችግር አለ ማለት ነው።

- አንዳንዴ የሃርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል።

- በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ጊዜ ራሙ ከኮምፒውተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው።

- ይህም ማለት ኮምፒውተሩ ከራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር፤ የራሱ
ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ ዓይነት ራም በአንድ ኮምፒዩተር ውስጥ ስንጠቀም ነው።

- ለምሳሌ 70ns ላይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል።

- ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ጊዜ Windows ክራሽ ያደርጋል።


፫. ባዮስ ሴቲንግ (BIOS Settings)

- እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል።

- እነዚህን ሴቲንጎች ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2
ወይም F10 እንጫናለን። (እንደ
ኮምፒውተሩ ይለያያል።)

- ኮምፒውተሩን ስንከፍት ከጥቂት ሰከንዶች
በኋላ F2ን ወይንም F10ን በመጫን ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል።

- ነገር ግን አንዴ ባዮስ ውስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።

- ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ማንሳት ወይንም ወረቀት ላይ ሴቲንጎቹን ማኖር፤ አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ ለመቀየር ያስችለናል።

- ብዙውን ጊዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው።

- የድሮ ኮምፒውተሮች ላይ ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ጊዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው።

- ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒውተሩ ክራሽ ያደርጋል
ወይም ፍሪዝ ይሆናል።


፬. ቫይረስ (Virus)

- ቫይረሶች የኮምፒውተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት
ወይም የኮምፒውተር ፋይሎች
ላይ በመጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ።

- ቫይረሶች የትዕዛዞች ስብስብ ሆነው እራሳቸውን በሌላ የኮምፒውተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ። (ብዙ ጊዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)

- ኮምፒውተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ኃይል ስላለው ኮምፒውተሩን
ክራሽ ወይም ፍሪዝ ሊያደርግ ይችላል።


፭. የሲፒዩ (CPU) መጋል

- በኮምፒውተራችን ውስጥ ካሉ ሃርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ (CPU ወይም Central Processing Unit) ነው።

- ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል።

- ሲፒዩ ብዙጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር፤ ከኮምፒውተራችን ጋር አንድ ላይ
ይመጣል።

- እነዚህ ቬንትሌተሮች ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒውተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል።

- ይህ ደግሞ በኮምፒውተራችን ላይ የ'ከርኔል ኢረር' (Kernel Error) ያስከትላል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube