Get Mystery Box with random crypto!

ዜግነቴ ኩራቴ #1 ፅናት ብዙ ጊዜ ስለመጣንበት መንገድ ፣ ስላሳለፍነው ህይወት እንዲሁም በዑደታች | Yezeginet Kibir

ዜግነቴ ኩራቴ #1
ፅናት

ብዙ ጊዜ ስለመጣንበት መንገድ ፣ ስላሳለፍነው ህይወት እንዲሁም በዑደታችን ስላጋጠሙን መሠናክሎች መለስ ብለን ስናስታውስ ቀድሞ ትውስታችንን የሚሞላው ምን ያህል ከባድ እና አስቸጋሪ እንደነበረ ነው፡፡ ነገር ግን ያንን ሁሉ አልፈነው እዚህ የደረስንበትን ጥንካሬአችንን እና ፅናታችንንም አብረን ማስታወስ አለብን፡፡

ከየአቅጣጫው ከህይወት የሚወረወርብንን ጦር በሙሉ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ፣ በብርታትም ውስጥ ይሁን በስንፍና ፣ በራሳችንም ይሁን በሌሎች ርዳታ መክተንም ይሁን አምልጠን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡

አያኮራም?

የነገውንም መሰናክላችንን እናልፍ ዘንድ የእስከዛሬውን ፅናታችንን መለስ ብለን እያየን ለነገ እንበርታ!

ዜግነቴ ኩራቴ!
የዜግነት ክብር