Get Mystery Box with random crypto!

እናንተዬ …. ኧረ እንዴት ከረማችሁ? በኹሉ ነገር መሐል እንኳን የደህንነት ምኞት እንካችሁ!!! | Yezeginet Kibir

እናንተዬ …. ኧረ እንዴት ከረማችሁ?
በኹሉ ነገር መሐል እንኳን የደህንነት ምኞት እንካችሁ!!!

መፅሔታችን 2ኛ ዕትም ደረሰች እኮ!

በመጀመሪያ ዕትማችን በሰጣችሁኝ ገንቢ እና አበረታች እንዲሁም ገሳጭ አስተያየቶች እንዴት እንደኮራሁ እና እንደተደሰትኩ ብታውቁ! …. ደስስስ ነው ያስባላችሁኝ፡፡ ይኸው ሁለተኛዋንም ለናንተ ለማድረስ ተፍ ተፍ እያልኩ ነው፡፡

የተለያዩ ጉዳዮችን ትዳስሳለች! ለዜጋው ይጠቅማል ፣ ያዝናናል ፣ ያስተምራል ፣ አዲስ ነገር ያስጨብጣል ፣ ያስተዋውቃል ፣ ይሞግታል ፣ ያስቃል ፣ ያስለቅሳል ……. ያልነውን ሁ….ሉ በሚመጥነን መልኩ በዓይነት በዓይነቱ እያሰነዳዳን ነውና …. እናንተም ይኼ ይጨመር ፣ ይኼ ሀሳብ ይነሳ … የምትሉትን በፌስቡክም ሆነ በቴሌግራም ወይም በኢሜይል ላኩልኝ!

ታሪካችንን እንከትብ ፣ ለቀጣይ ትውልድ መሠረት እናስቀምጥ ፣ በዕውቀት የዜግነታችንን ክብር እንጎናፀፋለን!!!

#የዜግነትክብር #መፅሔት #ሁለተኛእትም