Get Mystery Box with random crypto!

እናትን ........ አይጉደል ጎዳዋ፤ አይሸርከት እግሯ፤ እንዳታለቅስ ከፍቷት፤ ማጣት ቢያገኛት | የኛ getmoch🌹

እናትን
........


አይጉደል ጎዳዋ፤
አይሸርከት እግሯ፤
እንዳታለቅስ ከፍቷት፤
ማጣት ቢያገኛት፤
ሃዘን እንዳይገባት፤
ዳቦ አይ ራባት፤


ረጋጭሽ መንደር፡
መጥቼ ብዋቀስ፡ ጩኸቴን ባገነው፤
እናትን አይክፋት፡
እያልኩኝ ብማፀን፡ የሚሰማኝ ማነው??



ይሄ የሚታየኝ፡
ከፊት ለፊቴ ላይ ፡ስጋሽ የደቀቀው፤
እዚ ያደረሰሽን፡
የልብሽን ብርታት፡ መንገድሽን ባውቀው፤
እናትነትሽን ፡ ገብቶኝ እንዳፈቅረው።


ባይታደል ጎጆ፡
እንዲገባት ባትኖር፡ ቢያስድሃትም ልፋት፤
ተደስታ ትኑር፡
በምንም በማንም፡ እናትን አይክፋት።






ለኢትዮጵያውያን አንባቢያን ብቻ
በቻናላችን የተለያዩ
አጫጭር ግጥሞች
መጣጥፎች
ወጎችን
ማግኘት ይችላሉ።
ሀሳብ/አስተያየት ካለዎት?

@Natty2119 or @Yoditaniya
መስጠት ይችላሉ አንዳይሳቀቁ!