Get Mystery Box with random crypto!

በሁለት ክፍል ብቻ የሚያልቅ #___ተቃራኒ_ፍቅር በ(ንጉሡ ተሰማ(ጢያ)) | የተሰባበሩ ፊደላት

በሁለት ክፍል ብቻ የሚያልቅ

#___ተቃራኒ_ፍቅር
በ(ንጉሡ ተሰማ(ጢያ))
ክፍል አንድ

"ዲፓርትመንቱን ትፈልገዋለህ... ለምንድነው የማትገባው?"
የግንባሯ የደም ስሮች...ለክርክር ተወጣጥረዋል። የምትለው እየጠፋት ትግ ትግ ይላታል።
"አሁን ገና እየገባኝ ነው..!" ለንግግር እየተዘጋጀች።
"Biology ዲፓርትመንት እኔ ስለገባሁበት አስጠላህ። አይደል?"
ፈገግ ብሎ እንደ ማሾፍ እያለ...
"በግራ ከተነሱ አያድርስ ትላለች ሀያቴ... ምን ሆነሽ ነው? እንዴ.... እኔ Biologyን እወደዋለሁ እንጂ እኮ አልፈልገውም። የራስሽን መላምት እዛው አስቀሪው" እንደመቆጣት ብሎ እጁን እያወራጨ...
"እሺ እሱን ተወው። ... መጀመሪያ Biology በ1ኛ መርጬዋለሁ አልከኝ ግን ውሸት ነበር... ቀጠልክ የምትጠላውን የ physics department ገባህ ... ሰለስክ እወደዋለሁ እንጂ አልጠላውም አልክ።
ቢኒያም... ምንህም አልገባ ብሎኛል።"
ረጋ ለማለት እየሞከረ ... ወደፊት ጠጋ ብሎ ክንዶቹን ጠረጴዛው ላይ አስደግፎ...
"አንቺ ብትሆኝ ምን ታደርጊ ነበር..?"
"ማለት?... ምኑን? "
"ምሳሌ አንቺ እኔን ትወጂኛለሽ ... ነገር ግን ልታፈቅሪኝ አልቻልሽም ወይንም ደግሞ አልፈለግሽም።" ቀለል አድርጎ
"እርሱና ይሄ ምን ያገናኘዋል? ይሄ እኮ ለወደፊት የምትወድቅበት... የምትተማመንበት ነገር እኮ ነው።" ትኩር ብላ እያየችው....
"አይደል...? እውነትሽን ነው። እኔ እኮ አንቺን ለጊዜያዊ መጠቀሚያ እያሰብኩሽ ነበር... ለዛ'ም አይደል አራት ዓመት ሙሉ ስከተልሽ የኖርኩት ¡ " ቁጣው እጆቹን ከመቼው እንደሰበሰባቸው አላስታወሰውም።
"እኔ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም። ... ማለት የፈለኩት..." በእጁ እንድታቆም ምልክት ሰጣት።
በመካከላቸው ዝምታ ለትንሽ ጊዜ ንጉሥ ሆነ..............
"አውቃለሁ እንደማትወጂኝ... እንዳልሽውም አንቺም Biology ስለገባሽ ነው.... Biologyን ያልመረጥኩት። አንድ ክፍል ቁጭ ብሎ ከሚያፈቅሩት ሰው ጋር መቀመጥ... ያውም ፍቅርን ካልተረዳ... ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አፍቃሪ ነው የሚያውቀው።..." ዕንባ እየተናነቀው "...እንደውም እውነቱን ልንገርሽ... አሁን አሁን በጣም እያስጠላሽኝ ነው ¡ ለዛ ነው የማልችለውንና የማልወደውን የ physics ትምህርት የምማረው። በአንድ ሴሚስተር እንኳን ቢያባርሩኝ ብዬ..." ቃላቶቹ በአንደበት ወጥተው ወደ መክሊት ሊሄዱ አዳገታቸው። እልህ... ሮጦ አለመድረስ.... ፈልጎ አለማግኘት... አፍቅሮ መጠላት ተደማምረው የዛሬውን 'ቢኒያም'ን ፈጠሩ። በአንዲት እንስት ምክንያት ልፋቱን(የቤተሰብ፣ የጎረቤት፣ የዘመድ፣የጓደኞቹን) አራግፎ... ስለመሄድ የሚያስበውን 'ቢኒያም'።

መክሊት ቢኒያም ባወራው ንግግር ደንግጣ እንደፈዘዘች ነው... የምትለው ጠፋት። በሰዎች ተጠያቂ እንደሆነች ይሰማታል። ግን ያላፈቀሩትን ሰው ለሰው ተብሎ መቅረብ ፍቅር ነው? ብላ ከራሷ በሃሳብ ትሟገታለች። ግን እሱን ማረጋጋት መቻል አለባት።

"ይኸውልህ ቢኒያም... ያሰብከው የሞኝ ሃሳብ ነው..." አቋረጣት... መብረቅ ከሰማይ የወረዳ መሰላት
"ሁሌም እኮ ይባላል... አፍቃሪ ሞኝ ነው። እኔን ባትወጂኝ እንኳን እንደሌሎቹ ሰዎች ባትሆኚ ይሻል ነበር። ... እኔ እኮ ሳፈቅርሽ ከሌሎች ትለያለሽ ብዬ ነበር ያፈቀርኩሽ...እንደዛ ነበር የሚሰማኝ" ዕንባውን መቆጣጠር ተሳነው.......


..... ይቀጥላል



t.me/yetesebere