Get Mystery Box with random crypto!

በረመዳን ምን ይጠበቅብናል? (ክፍል 3) የቀልብ መስተካከል ምልክቶች ረመዳን የሚያመጣው የልብ | °♡•የረሱል ኡማ°♡•

በረመዳን ምን ይጠበቅብናል? (ክፍል 3)

የቀልብ መስተካከል ምልክቶች

ረመዳን የሚያመጣው የልብ ፅዳት ምንድን ነው?! ስትል ያየሁህ መሰለኝ። ልብ ውስጥ ያለው ኢማን ሲነቃቃ… ሥሮቹም ልብ ውስጥ ሲጠልቁ የልብ ፅዳት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ። ነብያችን እንዲህ ይላሉ፡-

ألا إن في الجسد مضغة إذا صلحت صلح الجسد كله، وإذا فسدت فسد الجسد كله ألا وهي القلب

“ንቁ! አካል ውስጥ ቁራጭ ሥጋ አለች። እርሷከተስተካከለች ሁሉም አካል ይስተካከላል። እርሷከተበላሸችም ሁሉ ነገር ይበላሻል። ንቁ እርሷም ልብናት!!”

የዚህን ልብ ባለቤት ለመልካም ሥራዎች ሲጣደፍ፣ የአላህን ዲን ምልክቶችን ሲያከብር ትመለከተዋለህ። አላህ እንዲህ ይላል፡-

ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى الْقُلُوبِ

“(ነገሩ) ይህ ነው። የአላህንም የሃይማኖት ምልክቶች የሚያከብር ሰው እርሷ  ከልቦች የኾነች ጥንቃቄ ናት።”

(አል-ሐጅ 22፤ 32)

የራስ ተነሳሽነቱ ያድጋል።

لَا يَسْتَأْذِنُكَ الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ أَن يُجَاهِدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ  وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالْمُتَّقِينَ

“እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትበገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው(ለመቅረት) ፈቃድን አይጠይቁህም። አላህም የሚፈሩትን ዐዋቂ ነው።” (አት-ተውባ 9፤ 44)

ለተግሳፅ እና ለመመሪያዎች በፍጥነት ይታዘዛል።

ذَٰلِكَ يُوعَظُ بِهِ مَن كَانَ مِنكُمْ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ

ዱንያን ችላ ሲል አላህ ዘንድ ላለው ምንዳ ሲሰስት ታየዋለህ። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

إذا دخل النور القلب أنشرح وأنفتح قالوا: يا رسول الله وما علامة ذلك؟ قال: الإنابة إلى دار الخلود والتجافى عن دار الغرور والإستعداد للموت قبل نزوله

“ብርሀን ልብ ውስጥ ሲዘልቅ ይሰፋል፤ ይከፈታል።” ባልደረቦቻቸውም “የዚህ ምልክት ምንድን ነው?” ብለውጠየቁ። “ወደ መዘውተሪያይቱ ዐለም መናፈቅ፣ ከመታለያይቱ  ዓለም  መራቅና ሞት ከመድረሱ በፊትመዘጋጀት።” አሉ፤ መልእክተኛው።

እንግዲህ ይህ ከሆነ የአላማችን መሳካት ምልክቱ አንድ ጥያቄ ብቻ ይቀረናል። አላማችንን እንዴት እናሳካዋለን?

ግባችን እውን የሚሆንባቸውን አማካዮች (means/ ወሳኢል) እናውቃቸዋለን። እንደውም አብዛኞቹን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ተግብረናቸዋል። አዲሱ ነገር እንዴት እንጠቀምባቸው የሚለው ነጥብ ነው። ረመዳን ውስጥ ለሚታሰቡት ዓላማዎች እንዴት እናውላቸው የሚለው ጥያቄ ነው አሳሳቢው። እነዚህን አማካዮች (means/ ወሳኢል) ለሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን።

አንደኛው ክፍል አንድ ባሪያ በርሱና በጌታው መሀል ያለን ችግር የሚያስተካክልበት ነው። አብዝሀኛ ትኩረቱም የመንፈስ እድገቱን የሚያበለፅጉት ላይ ነው።

ሁለተኛው ክፍልም አንድ ባሪያ ከማህበረሰቡ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ዙሪያ ያሉትን ነገሮች የሚያስተካክሉለት አማካዮች ናቸው።

ከእነዚህ ክፍሎች መሀል አንዱን ይዞ ሌላኛውን መተው አይበቃም። ሁለቱም የሙስሊምን የምድር ሚና የሚያሟሉ መሠረታዊ ነጥቦች ናቸው። አላህ እንዲህ አለ፡-

وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا

“እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምንም  መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ  ሃይማኖቱ  ያማረ ማን ነው? አላህምኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው።”  (አን-ኒሳእ 4፤ 125)

ፊትን ለአላህ መስጠት መንፈሳዊና ከስሜት ጋር የተገናኘ ነገር ነው። ነገር ግን ለፍጥረት መልካም መዋል ሊከተለው ይገባል። አንዳንድ ሰዎች ግን ይህን ስተውታል። ለአንዱ ትኩረት ሰጥቶ ሌላውን ትኩረት ይነፍገዋል። ሙሉ ትጋቱን በርሱና በፈጣሪው መሀል ያለውን ርቀት ለማጥበብና ግንኙነቱን ለማስተካከል በማዋል ጥቅሙ ለሠዎች የሆነን ተግባር የተወ ሰው ኢማኑ ጎዶሎ ነው።

ኢማን ንግግርና ተግባር ነው። መልካም ሥራዎች የመልካም ሠሪውን ኢማን ይጨምራሉ። የኢማኑን መሠረቶችም ልብ ውስጥ ያሰርፃሉ። አላህ እንዲህ አለ፡-

إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُهُ

“መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል። በጎ ሥራም ከፍያደርገዋል።” (ፋጢር 35፤ 10)

የአንዳንድ ቀደምት ሙስሊሞች ዘገባ ላይ የተገኘ ንግግርን እናድምጥ። እንዲህ ይላል፡-

إن العبد إذا قال لا إله إلا الله بنية صادقه نظرت الملائكة إلي عملة، فإن كان موافقاً لقوله، صعدا جميعاً، وإن كان العمل مخالفاً وقف قوله حتى يتوب من عمله

“አንድ የአላህ ባሪያ በንፁህ ኒያ ‘ላኢላሀ ኢል–ለ–ሏህ’ሲል መላኢካዎች ሥራውን ይመለከታሉ። ተግባሩናንግግሩ ከተጣጣሙ በአንድ ላይ ይዘዋቸው ያርጋሉ።ተግባር ከንግግር የተለየ እንደሆነ ከተግባሩእስከሚቶብት ድረስ ንግግሩ እዚሁ ይቆያል።”

በአንፃሩ በሰዎች መሀል የሚደረጉ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ላይ መጠመድ፣ የሰዎችን ጉዳይ ለመፈፀም የሚደረግ ሩጫ፣ ችግራቸውን ለመፍታት የሚደረግ ርብርብ፣ ሰዎችን ለመርዳትና ለመጥቀም የሚሠራ ሥራ ከአላህ ጋር ግንኙነት ካለው ልብ ካልመነጨ አደጋ አለው። ምናልባትም በመልካም ሠሪው ልብ ውስጥ አሉታዊ ተፅእኖ ሊፈጥር ይችላል። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ፡-

مثل الذي يعلم الناس الخير، وينسى نفسه مثل الفتيلة، تضيء للناس وتحرق نفسها

“ለሠዎች መልካምን ነገር እያስተማረ ነፍሱን የሚዘነጋልክ እንደ ሻማ ነው። ለሠዎች እያበራች እራሷንታነዳለች።”

አል-ራፊዒይ እንዲህ ይላሉ፡-

إن الخطأ أكبر الخطأ أن تنظم الحياة من حولك وتترك الفوضى في قلبك

“ከስህተት ሁሉ ትልቅ ስህተት የሠዎችን ህይወትእያሳመርክ የራስህን ልብ ማዝረክረክ ነው።”

ስለዚህ ሁለቱም ነገሮች በአንድነት መኖር አለባቸው።

#ይቀጥላል

----------
{ምንጭ ↣ ethiomuslims.net }
——————————————————————
«በብዕርህ መጣራት ባትችል በሰዎች ብዕር ተጣራ»

Join us ☞ @worldmuslims