Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች ያለ ሀኪም ትዕዛዝ በመውሰድ በጀርሞች መላመድ የተነሳ ከፍተ | YeneTube

በኢትዮጵያ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች ያለ ሀኪም ትዕዛዝ በመውሰድ በጀርሞች መላመድ የተነሳ ከፍተኛ የጤና ስጋት መደቀኑ ተገለፀ

መድኃኒቶችን ያለ ሀኪም ትእዛዝ መሸጥና መጠቀም ሁኔታውን ካባባሱት ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ ነው ተብሏል።

በኢትየጵያ የፀረ ተህዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድ ትልቁ የጤና ስጋት በመሆኑ ችግሩን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት አስፋላጊ መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ  የመድሃኒት መረጃና አግባባዊ አጠቃቀም ዴስክ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም እሸቴ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ የመድኃኒት ባለሙያዎች ማህበር ጋር  በመተባበር የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል።

የስልጠናው ዓላማ  አቅምን በማሳደግ የተሻለ የጤና ግብዓት ማቅረብ እንደሆነ ገልፀው ተቋሙ ከሌሎች ባለድርሻ  አካላት ጋር በመተባበር ብሄራዊ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስትራቴጂ ነድፎ በተግባር ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሀኪሞች ተገቢውን መድኃኒት ማዘዝ እና  የፋርማሲ ባለሙያዎችም  በሀኪም የታዘዘውን መድኃኒት በአግባቡ በማደል የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ይቀንሳል  ተብሏል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ትልቁ የጤና ሰጋት እና ክስተት የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ እንደሆነ አቶ ኃይለማርያም  ጠቁመው ይህንን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር  በመሆን መስራት እንደሚኖርባቸው አስረድተዋል።በስልጠናው የተመረጡ የግል የመድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች ፣ የመድኃኒት ባለሙያዎችና የእንስሳት መድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች የመድኃኒት ባለሙያዎች በስልጠናው እንዲሳተፋ ተደርጓል፡፡

አሥራ ሁለተኛው የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ቀን በዛሬው እለት  የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  የመንግስት እና የግል  ዘርፍ አጋርነት ማጠናከር  በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።


Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa