Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባካሄደው የመልካም አስተዳደር ምዘና፤ የማዕድን ሚኒስቴር “ዝቅ | YeneTube

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባካሄደው የመልካም አስተዳደር ምዘና፤ የማዕድን ሚኒስቴር “ዝቅተኛ አፈጻጸም” ማስመዝገቡ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ያለውን “መልካም አስተዳደር አፈጻጸም” በተመለከተ ላለፉት 10 ወራት ባደረገው ምዝና፤ የማዕድን ሚኒስቴር “ዝቅተኛ አፈጻጸም” ማስመዝገቡን አስታወቀ። የማዕድን ሚኒስቴር አፈጻጸሙ ዝቅ ያለው፤ የተቋቋመበት አዋጅ “የተሟላ ስልጣን እና ኃላፊነት ለሚኒስቴሩ የማይሰጥ በመሆኑ” ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል። 

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፤ የመንግስት አስፈጻሚ አካላት በአዋጅ የተሰጣቸንው ተግባራት “ጥራት፣ ቅልጥፍ እና ግልጽነት ባለው መንገድ” እየሰሩ መሆናቸውን የመከታተል እና የመቆጣጠር ስልጣን አለው።

ተቋሙ የማዕድን ሚኒስቴርን ጨምሮ በ15 የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ ከየካቲት 3፤ 2015 ጀምሮ ለ10 ወራት የቆየ “የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም” ምዝና ማከናወኑ ተገልጿል። 

ተቋሙ ምዝነናውን ለማከናወን የተጠቀማቸው፤ “ተጠያቂነት፣ ግልጽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ለህግ ተገዢነት እና ውጤታማነት” የሚሉትን የመልካም አስተዳደር መለኪያዎች ነው። 

በእነዚህ መለኪያዎች የተሻሻለ አፈጻጸም በማምጣት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ የያዙት የገንዘብ፣ የትምህርት እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ናቸው። የግብርና፣ የጤና እና የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተከታዮቹን ደረጃዎች አግኝተዋል።

“መሻሻል የሚገባው” በሚለው ምድብ በብቸኝነት የተቀመጠው የማዕድን ሚኒስቴር ነው።

ዝርዝሩን ለማንበብ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13258/

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa