Get Mystery Box with random crypto!

የእውነተኛ መንፈሳዊ አፍቃሪ ተግባሮች 1. ✓ በሃይማኖታዊ ስርዓት እንሂድ ብሎ ይመራታል። 2. | የመዝሙር ደብተር™

የእውነተኛ መንፈሳዊ አፍቃሪ ተግባሮች

1. ✓ በሃይማኖታዊ ስርዓት እንሂድ ብሎ ይመራታል።
2. ✓ ቃለ እግዚአብሔር እንማር ይላታል።
3. ✓ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንመን ይላታል።
4. ✓ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን እንጋባ ይላታል።
5. ✓ ለቃሉ ታማኝ ይሆናል።
6. ✓ ጥፋተኛ ሆኖ እራሱ ይቅርታ ይጠይቃል።
7. ✓ ፈገግታዋን ሳያበላሽ ሁሌ የፍቅረኛውን ስህተት ያርማታለ።
8. ✓ መንፈሳዊ ነገሮችን ያስተምራታል።
9. ✓ ሌላ ሴት ጋር አይሄድም ፍቅረኛውን አይዋሻትም።
1ዐ. ✓ በገንዘብ ጉዳይ አይጨነቅም እንደውም ያለን ይበቃናል ይላለ በቀና መንገድ ለማድረግ ይጥራል።
11. ✓ ለሌላ ሴቶች ፍቅረኛ እንዳለችው ይናገራል።
12. ✓ እራሱንና ፍቅረኛውን ይጠብቃል ያስከብራል።
13. ✓ የወደፊት እቅዱንና ዓላማውን ያወያያታል።
14. ✓ በነገሮችና በጨዋታዎች ሲግባቡ አፈቅርሻለሁ በማለት ፍቅሩን ይገልጽላታል።
15. ✓ ለፍቅረኛው ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ወደኋላ አይልም።
16. ✓ እውነተኛ አፍቃሪ ፍቅረኛውን ለቤተሰቡ ያስተዋውቃታል።
17. ✓ የፍቅረኛውን ስሜት በጥንቃቄ ይረዳል።
18. ✓ ፍቅረኛው የምትሰጠውን ሀሳብ በትዕግስት ያዳምጣል።
19. ✓ ፍቅረኛው ስትበሳጭ ምን ሆና ነው ስህተቴ ምንድን ነው ብሎ እራሱን ያርማል።
20. ✓ በስርዓተ ቤተክርስቲያን ያገባታል።
21. ✓ ውጫዊ መልኳን ሳይሆን ውስጣዊ ውበቷን ያደንቅላታል።

እግዚአብሔር እውነተኛ ፍቅር ይስጣችሁ

አሜን! በሉ ሰው የአፉን ፍሬ ይበላልና
t.me/yemezmurdebiter
t.me/yemezmurdebiter
t.me/yemezmurdebiter