Get Mystery Box with random crypto!

የጁቤ ጤና መረጃ Yejubie Health Information

የቴሌግራም ቻናል አርማ yejubietenamerja — የጁቤ ጤና መረጃ Yejubie Health Information
የቴሌግራም ቻናል አርማ yejubietenamerja — የጁቤ ጤና መረጃ Yejubie Health Information
የሰርጥ አድራሻ: @yejubietenamerja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-13 07:04:43 #የማህፀን_እባጭ
(Uterine Myoma) እና
#እርግዝና

#የማህፀን_እባጭ(#Myoma/fibrinoids) ከማህፀን ጡንቻ የሚነሱ ከፍተኛ ችግር የማያስከትሉ የማህፀን ላይ እባጮች ወይም እጢዎች ናቸው።
ባብዛኛው ምልክት የለሽ ሲሆን በድንገት ለሌላ ጉዳይ አልትራሳውንድ ወይም ሲቲ ስካን ሲነሳ ሊታይ ይችላሉ።

የማህፀን እባጭ ከእርግዝና በፊት መጠኑ የበዛ ከሆነና ቱቦች ከዘጋ እርግዝና ይከለክላል። ይህም ሲባል ከመቶ እባጭ ካላቸው እናቶች ከ1-2 በመቶ ብቻ የሚሆኑት እንደምክንያት ሊነሳ ይችላል።

የማህፀን የውስጥ ግርግዳ ላይ የወጣ እባጭ ደግሞ ተደጋጋሚ ውርጃን (#RPL) በማምጣት ይታወቃል። ይህም የሚሆነው የማህፀን ግረግዳ እንዲኮማተር እና የፅንሰት መጣበቅ(#implantation) እንዳይኖር ያደርጋል።

መጠኑ ትላልቅ እና ብዛት ያለው የማህፀን እባጭ በእርግዝና ወቅት የሚከተሉት ውስብስብ ችግሮች ሊያስከትል ይችላል።
1. የእባጭ ጠባይ መቀየር(#red degeneration):
እርግዝናው እያደገ ሲመጣ ማህፀን እና እባጩ እያደጉ ይሄዳሉ። በዚህም ወደ እባጩ የሚሄደው የደም ዝውውር በቂ ካለመሆን የተነሳ ዕጢው ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ህመምን ያስከትላል።
2. የፅንስ ያቀማመጥ ችግር ያስከትላል፡ ፅንሱ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ በማገድ ትክክለኛ ያልሆነ አቀማመጥ(#malpresentation) እና አመጣጥ(#malposition) እንዲኖረው ያደርጋል።
3. የፅንስ እድገት መስተጓጎል(#IuGR)ያስከትላል
3.የማህፀን በር መዝጋት ያመጣል(#Tumor previa)፡ እባጩ የታችኛው የማህጨፀን ክፍል የያዘ ከሆነ የማህፀን በር በመዝጋት ለኦፕራሲዮን(#cs) ያጋልጣል።
4.የምጥ መርዘም(# prolonged labor)ያስከትላል: የማህፀን ጡንቻዎች በሚፈለገው መጠነ ቁርጠት የማምጣት አቅም በመቀነስ ለረዘመ ምጥ ምክነያት ሊሆን ይችላል።
5. ከወሊድ በኋላ ለከፍተኛ ደም መፍሰስ(#PPH) ያጋልጣል።
103 viewsAbebaw11, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 07:03:47
103 viewsAbebaw11, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 18:07:40 #ሄፓታይተስ_ቢ (#HEPATITIS_B)

ተላላፊ የሆነ በ ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ አማካይነት የሚከሰት በሽታ ነው። በጊዜ ሂደት ውስጥ ከባድ የሆነ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። ቫይረሱ አንዳንድ ሰዎችን በጣም ሊያሳምማቸው ይችላል። ይህ በሽታ በአብዛኛው የአለማችን ክፍሎች ኢትዮጵያንም ጨምሮ ይገኛል።

#እንዴት_ይተላለፋል?
ሰዎች ቫይረሱ ከተሸከመ ሰው ደም ጋር ሲነካኩ ሄፓይተስ ቢ ይይዛቸዋል። ሄፓታይተስ ቢ ከተያዘች እናት ወደ ልጇ በወሊድ ወቅት ሊተላለፍ ይችላል። ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት በማድረግም ሊተላለፍ ይችላል።

ብዙ ሰዎች ሄፓታይተስ ቢ እያለባቸው ለብዙ አመታት ህመም ሳይሰማቸው ሊኖሩ ይችላሉ። በጊዜ ሂደት ውስጥ ለጉበት መበላሸት፧ ለጉበት ስራ ማቆም እና ለጉበት ካንሰር ሊዳርግ ይችላል።

    ሰዎች ሄፓታይተስ ቢ እንዳለባቸው እንዴት ያውቃሉ?
  
      ብቸኛ መንገድ የደም ምርመራ ሲያደርጉ ነው።   ይህ ከእጅ ላይ ደም በመውሰድ የሚደረገ ቀላል ምርመራ ነው። አንድ ነብሰጡር አናት በእርግዝና ወቅት ምርመራ ማድረገ ግድ ይላታል።

      ሰዎች ሄፓታይተስ ቢ እንዳለባቸው ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።  ሄፓታይተስ ቢ እንዳለባቸው የሚያውቁ ሰዎች ቫይረሱ ወደ ሌላ ሰው አንዳይተላለፍ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ፣ ማለትም ኮንዶምን መጠቀም። ዋንኛው የመከላከል መንገድ ክትባት መውሰድ ነው። ሄፓታይተስ ቢ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ እናቶች በእርግዝና ወቅት ወደ ጤና ተቋማት በማቅናት የእርግዝና ክትትል እንዲያደርጉ ማድረግ እና ስለ በሽታው ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል። ሆፓታይተስ ቢ ቫይረስ ካለባት የተወለደ ህፃን በተወለደ በ12 ሰዓት ውስጥ መከተብ እለበት።
100 viewsAbebaw Mebratu, 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 17:18:07 #ሾተላይ (RH-Incompatablitiy) ምንድን ነው?

ሾተላይ በመባል የሚታወቀው ክስተት ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት ነው።

ይህ ለምን ይሆናል?

የሰዎች ደም በአራት መደብ ይከፈላል(A, B, AB, O) እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ፡ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) እና አር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-)። ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል። የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን። ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።

ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ ደሟ ውስጥ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የሆኑ የደም ህዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል። ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።

በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል። የደም ዓይነቱ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን በጤና ይወለዳል። ይህ እንዲሆን ግን
የአባትየው የደም ዓይንት አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) መሆን አለበት?

ሕክምናው

የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት።

በደሟ ውስት ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽነሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።

በሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል።

እንዴት እንከላከለው?

ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።

የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።

እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት ምርመራ (indirect coomb’s test) ንጥረ-ነገሩ አለመመረቱን ያረጋግጣል። እዳይመረት የሚከላከል መድኃኒት (Anti-D) 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል። ከወለደች በኃላ የልጇ የደም ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።

እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት።

እባኮዎን join ያድርጉ
83 viewsAbebaw Mebratu, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 17:18:05
81 viewsAbebaw Mebratu, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 16:57:50 #የጨጓራ_አንጀት_ቁስለት_ምንድነው? #ምክንያቶቹስ?

የጨጓራ_አንጀት ቁስለት ዋነኛ ምክንያቶች ሁለት ናቸው ፡ ፡ አንደኛው በተለምዶ የጨጓራ ባክቴሪያ የሚባለው  ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ዘርፍ የሆኑት Non-steroidal anti-inflammatory drugs ናቸው ፡ ፡ የ H pylori ባክቴሪያ በታዳጊ ሀገሮች በስፋት የተሰራጨ ሲሆን በአገራችንም በርካታ ሰዎች ባክቴሪያው ይገኝባቸዋል ፡ ፡
ሁለተኛ የተጠቀሱት የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ሲሆኑ በተለምዶ ሰዎች የሚወስዳቸውን Advil ( Ibuprofen), Diclofenac እና የመሳሰሉትን ያካትታል ፡ ፡ እነዚህን ሰዎች በስፋት አንዳንዴም ያለሃኪም ትዕዛዝ ለራስ ምታት ፤ ለቁርጥማት፤ ለጀርባ ህመም እና መሰል ችግሮች ይወስድዋቸዋል ፡ ፡ ሆኖም እነዚህ መድሃኒቶች የጨጓራ አሲድ መከላከያዎችን ስለሚያከሽፉ አንዳንዴ የጨጓራ ቁስለት ሊያመጡ ይችላሉ ፡ ፡

#የጨጓራ_መቁሰል_ምልክቶች

ሰዎች የጨጓራ ቁስለት ሲኖራቸው በአብዛኛው የሆድ ክፍል ላይ ተደጋጋሚ ህመም ያጋጥማቸዋል ፡ ፡ ይህም በሁለቱ ግራና ቀኝ ጎድኖች መሃል ከእምብርት ከፍ ብሎ ያለውን ቦታ በዋነኝነት ያካትታል ፡ ህመሙ እየተባባሰ ሲመጣ ማስታወክ ሊመጣ ይችላል ፡ ፡ ሲከፋ ደግሞ ደም የቀላቀለ ማስታወክ ሊከሰት ይችላል ፡ ፡ እዚህ ላይ ደም ማስታወክ ስንል ንፁህ ቀይ ደም ብቻ ሳይሆን አንዳንዴም ጥቁር የቡና አተላ መሰል ( ደም ከአሲድ ጋር በመቀላቀል የሚፈጠር ) ሊሆን ይችላል ፡ ፡ ይህ ጥቁር ደም አንዳንዴም አንጀት ውስጥ በመቆየት ምክንያት ከሰገራ ጋር ሊወጣ ይችላል ፡ ፡

#ምርመራ

የጨጓራ ህመም ሲኖር ወደ ጤና ተቋም ጎራ ብሎ መታከም ያስፈልጋል ፡ ፡  ቀለል ያለ ችግር ከሆነ ብዙ ጊዜ ጥቂት ምርመራዎችን በማድረግ በመድሃኒት ማከም ይቻላል ፡ ፡ በጠና ለታመሙ ፤ እድሜያቸው ለገፋ እንዲሁም የደም መድማት ላላቸው ሰዎች ግን የኢንዶስኮፒ ምርመራ በተለምዶ ያስፈልጋል ፡ ፡ የኢንዶስኮፒ ምርመራ ማለት በቀጭን ቱቦ መልክ በተሰራ ካሜራ ወደ ጨጓራ ዘልቆ በመግባት ውስጣዊ የጨጓራና አንጀት ክፍል መመልከት ማለት ነው ፡ ፡ በዚህ ምርመራ የቁስሉን ጥልቀት እና ስፋት ግፋ ሲልም የሚደሙ ቁስሎችን ማስቆም ይቻላል ፡ ፡

#ህክምና

ብዙ ሰዎች ለቁስለት ህክምና በሚሰጡ መድሃኒቶች ይድናሉ ፡ ፡ ለዚህም ተብሎ የተዘጋጁ የአሲድ ምርትን የሚቀንሱ መድሃኒቶች በስፋት በገበያ ላይ ይገኛሉ ፡ ፡ የጨጓራ ባክቴሪያ ከተገኘ ደግሞ በፀረ ተህዋስ መድሃኒቶች ( Antibiotics ) መታከም ይቻላል ፡ ፡

#መከላከያ

መሰል የጨጓራ ችግርን ለመከላከል ከሚረዱ ነገሮች አንዱ አስፈላጊ ያልሆኑ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ከመውሰድ መቆጠብ ነው ፡ ፡ እነዚህ መድሃኒቶች ከተወሰዱም ከተፈቀደው መጠን በላይ አለመውሰድ ይመከራል ፡ ፡ ምግብ እና ውሃንም ንፅህና በጥንቃቄ በመጠበቅም ከጨጓራ ባክቴሪያ መከላከል ይቻላል ፡ ፡
200 viewsAbebaw Mebratu, 13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 16:57:41
193 viewsAbebaw Mebratu, 13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 17:09:49 https://www.moh.gov.et/site/sites/default/files/2022-10/List%20of%20CPD%20Providers%20as%20of%20September%202022.pdf

የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ሥልጠና (CPD) እንዲሠጡ የተፈቀደላቸው ተቋማት ዝርዝር

MoHE
198 viewsAbebaw, 14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 07:17:17 #የዘራኸውን_ታጭዳለህ

አይምሮህ ውስጥ ምንድነው የምትዘራው? መልካም ሀሳብ ወይ መጥፎ ሀሳብ? አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ፤ የዘራኸውን ታጭዳለህ! ደጋግመህ ያሰብከው ሀሳብ በህይወትህ ውስጥ በተግባር ይገለጣል።

ከሚያበረታቱህ ሰዎች ጋር ብቻ ዋል፤ በጎ ነገር ብቻ ስማ፤ ብቻህን ስትሆን ራስህን አድንቅ፤ እንደምትችል ለራስህ ንገረው፤ አየህ ጠንካራ ስብዕና የሚገነባው እንደዚህ ነው።
174 viewsAbebaw, 04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ